መስከረም 8 2018 -መጪው የበጋ የአየር ጠባይ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሚኖርባቸው አካባቢዎች በደረሱ ሰብሎች ላይ ተጽዕኖ ሊያደርስ ይችላል ተባለ።
- sheger1021fm
- 30 minutes ago
- 1 min read
ይህን ያለው የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ነው።
ኢንስቲትዩቱ በበጋው የአየር ሁኔታ በሚኖር ወቅቱን ያልጠበቀ #ዝናብ በትግራይ፣ አማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ አካባቢዎች በደረሱ ሰብሎች ላይ ተጽዕኖ ሊያደርስ ይችላል ብሏል፡፡
ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት አከባቢዎች የዝናብ መቆራረጥ ሊኖር እንደሚችልም ተጠቁሟል።
ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንደ ቦረናና ጉጂ ዞኖች፣ ሲዳማ እና ደቡብ ኢትዮጵያ መደበኛ ዝናብ የሚኖራቸው መሆኑን ኢንስቲትዩቱ ተናግሯል።
የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል ደግሞ ከመደበኛ በታች የሆነ የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚያገኙ ተጠቁሟል።

በሌላ በኩል የምዕራብና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚያገኙም ተነግሯል።
ኢንስቲትዩቱ ግንቦት ላይ የሰጠው የክረምት ወቅት የአየር ጠባይ ትንበያ መሬት ላይ ከተከሰተው ጋር የተጣጣመ እንደነበረም ተነግሯል፡፡
ማህበረሰቡ የደረሱ ሰብሎችን በወቅቱ እንዲሰብሰቡ ማድረግ ከመደበኛ በታች ዝናብ በሚስተዋልባቸው የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል የሚገኘውን የዝናብ መጠንና ስርጭት በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል ሲል ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል።
ፍቅሩ አምባቸው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
Comments