መስከረም 7 2018 - ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ለመተግበር ከስትራቴጂ ዝግጅት እስከ ታሪፍ ህትመት ያሉ ስራዎችን ጨርሳለች ተባለ።
- sheger1021fm
- Sep 17
- 1 min read
በጣም ባጠረ ጊዜ ይፋዊ በሆነ ሥነ ሥርዓት የንግድ ስምምነቱን ተግባራዊ ማድረግ እንደምትጀምርም የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተናግሯል።
የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነትን በመፈረም እና በፓርላማ በማፀደቅ ከቀዳሚዎቹ ሀገራት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ ግብይት እንዴት ይፈጸማል? አሰራሩስ በምን የህግ ማዕቀፎች ይመራል የሚሉ እና መሰል ጉዳዮችን የያዘ የትግበራ ስትራቴጂ ማዘጋጀቷ ተነግሯል።
የቀረጥ ሥርዓት የሚመራበት ሰነድም እንዲሁ በገንዘብ ሚኒስቴር መዘጋጀቱን ሠምተናል።
ስምምነቱን ባጠረ ጊዜ ይፋዊ በሆነ ሥነ-ሥርዓት ተግባራዊ ማድረግ እንደምትጀምር የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ አቶ ወንድሙ ፍላቴ ነግረውናል፡፡
ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ስምምነቱ ተግባራዊ ሲሆን ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት አቅማቸውን ማሳደግ አለባቸው ያሉት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚው መስሪያ ቤታቸውም አዳዲስ አሰራሮች እንዲተዋወቁ እየሰራ እንደሚገኝ ነግረውናል፡፡
የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ሙሉ ለሙሉ ስራ ላይ ሲወል በአህጉሩ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ ወደ 33 በመቶ ያሳድገዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
አሁን ያለው የሀገራቱ የንግድ ልውውጥ ከ11 በመቶ እንደማይበልጥ ተነግሯል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ንጋቱ ረጋሣ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments