top of page

መስከረም 3፣2017 - ‘’በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች እየተካሄዱ ያሉት የትጥቅ ግጭቶች አላማቸው አልገባኝም’’ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት

  • sheger1021fm
  • Sep 13, 2024
  • 1 min read

Updated: Sep 14, 2024

መስከረም 3፣2017


''በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ያሉ ግጭቶች በዘላቂነት ለማስቆም፤ ከሁሉም ወገን ሀቀኛ ፍላጎት አላየሁም'' ሲል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ተናገረ፡፡


በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች  በመንግስት እና በታጣቂዎች መካከል እየተደረገ ያለው ግጭት ዓላማው ሊገባኝ አልቻለም ሲልም አስረድቷል፡፡


በሁለቱ ክልሎች ያለ መፍትሄ የቀጠለው ግጭት የጋራ ምክር ቤቱን በእጅጉ አሳስቦታል ያሉን የምክር ቤቱ ዋና ሰብሳቢ  ደስታ ዲንቃ ናቸው፡፡


ንጹሃንን እየገደለ፣ እያሰቃየ እና የሀገርን ሀብት እያወደመ ያለውን ግጭት ሁለቱም አካላት ቆም ብለው አስበው ምን እንዳመጣ እራሳቸውን ሊጠይቁ ይገባል ብለዋል ዋና ሰብሳቢው፡፡


ንጹሃን፣ ባለስልጣናት እና የባለስልጣና ልጆች እየተገደሉ እየታፈኑ ነው ያሉት የጋራ ምክር ቤቱ ዋና ሰብሳቢ ደስታ ዲንቃ በዚህ ጦርነት ውስጥ ማን እየተጠቀመ እንዳለ ማወቅ አልቻልኩም ሲሉ አስረድተዋል፡፡


“በጦርነቱ እንደ ሀገር ሀገር እየተጎዳ ነው፣ እንደ ህዝብ ህዝብ እየተጎዳ ነው ፣እንደ ዜጋ ዜጎች እየተጎዱ ነው ፣እንደ ታሪክ ታሪክን እያበላሽን ነው ምን ዓይነት ስሌት አስልተን እንደምንረጋጋ አላውቅም” ብለዋል፡፡


በሀገሪቱ በመንግስት እና በታጣቂዎች መካከል እየተደረገ ያለው ግጭት ውድመት እያስከተለ ቀጥሏል ያሉት አቶ ደስታ ዲንቃ ችግሩን በንግግር ለመፍታት በሁለቱም ወገን ፍላጎት አይታይም ሲሉ ወቅሰዋል፡፡


“አንዱ በአንዱ ላይ የበላይ ለመሆን ከሚደረግ ሩጫ የዘለለ ግጭቱን በንግግር የመፍታት ፍላጎት እየተመለከትን አይደለም” ሲሉ  ሰብሳቢው አቶ ደስታ ዲንቃ አስረድተዋል፡፡


ታጣቂዎችም ሆኑ መንግስት ችግሩን በንግግር ከመፍታ ይልቅ ግጭቱን ስም ለማጠልሸት አንዱ ሌላውን ለመወንጀል እና የህዝብ ድጋፍ ለማግኝት እየተጠቀሙበት ነው ሲሉ ሰብሳቢው ተናግረዋል፡፡


ምክር ቤቱ በመንግስት እና በታጣዊዎች መካከል እየተካሄደ ያለው ግጭት ሁለቱም አካላት እቆምለታለሁ፣ እቆረቆርለታለሁ የሚሉትን ህዝብ እና ሀገርን እያወደመ መሆኑን አውቀው በንግግር ችግራቸውን እንዲፈቱ ጠይቋል፡፡




ያሬድ እንዳሻው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page