መስከረም 29 2018 - ኢትዮጵያ ዛሬ የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነትን በይፋ ትቀላቀላለች።
- sheger1021fm
- Oct 9
- 1 min read
ዛሬ ከሰዓት በኋላ የተለያዩ ምርቶች በየብስ እና በአየር በይፋዊ ስነ ስርዓት ወደ ተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት እንደሚሸኙ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ነግሮናል
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ አቶ ወንድሙ ፍላቴ ይህንኑ ነግረውናል።
በአየር ትራንስፖርት የስጋ፤ የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶች ወደ ተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት እንደሚላኩ ተናግረዋል።
ይሄኛው የንግድ ልውውጥ በምስራቅና በደቡብ አፍሪካ ሀገራት ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ተጠቅሷል።
በየብስ ትራንፖርት ደግሞ ቡና፣ የጥራጥሬ ምርቶችና የቅባት እህሎች ወደ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ወደ ደቡብ አፍሪካ ይላካሉ ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ለመተግበር ሰፋ ያለ ዝግጅት ስታደርግ እንደቆየች ተጠቅሷል።
የንግድ ሂደቱን ተግባራዊ ለማድረግ በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሚመራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሲሰራ ቆይቷል ተብሏል።
ኮሚቴው የገንዘብ ሚኒስቴር ፤ የገቢዎች ሚኒስቴር ፤ የጉሙሩክ ኮሚሽን ፤ ብሄራዊ ባንክ ፤ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ፤ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ፤ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ፤ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የግል ዘርፍ ተወካዮችን የያዘ መሆኑ ተነግሯል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ንጋቱ ረጋሳ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s
👔LinkedIn ፡ https://tinyurl.com/tyfaekvx











Comments