top of page

መስከረም 29 2018 - በ2016 ዓ/ም 8,854 የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች የደረሱ ሲሆን ይህ አሃዝ በ2017 ዓ.ም ወደ 13,496 ከፍ ብሏል፡፡

  • sheger1021fm
  • Oct 9
  • 1 min read

በተጠናቀቀው 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ በሚገኙ ተቋማት ላይ ከ13,000 በላይ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች መደረጋቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ተናገረ።


በ2016 ዓ/ም 8,854 #የሳይበር_ጥቃት ሙከራዎች የደረሱ ሲሆን ይህ አሃዝ በ2017 ዓ.ም ወደ 13,496 ከፍ ብሏል፡፡


የሳይበር ጥቃት ሙከራዎቹ ድረ ገፆችን ከማስተጓጎል እና ከማቋረጥ የዘለለ እምብዛም ጉዳት እንዳላደረሱም ሰምተናል።


የሳይበር ጥቃቱ እየጨመረ የመጣበት ምክንያትም ድጅታላይዜሽን አሰራሮችን በሀገሪቱ እየተስፋፉ በመምጣታቸው እንደሆነ አስተዳደሩ ተናግሯል።


በሌላ በኩል የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሳይበር ደህንነት ወርን ከጥቅምት 1 እስከ ጥቅምት 30/2018 ዓ/ም ድረስ በተለያዩ መርሃ ግብሮች እንደሚያከብር ተናግሯል።


የሳይበር ደህንነት ወሩ “የሳይበር ደህንነት - የዲጂታል ኢትዮጵያ መሰረት" በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚከበርም ሰምተናል።


6ኛው የሳይበር ደህንነት ወር በሃሰተኛ መረጃ ዝግጅት፣ ቁጥጥርና ስርጭት ላይ እና በዲጂታላይዜሽን ደህንነት ላይ ትኩረት እንደሚያደርግም ተነግሯል።


ፍቅሩ አምባቸው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page