top of page

መስከረም 22 2018 - ለአገልግሎት የሚሆኑ ምርቶችና ቁሶች ከአካባቢ ስነ ምህዳር ጋር የተጣጣሙ እንዲሆን እና ከአንድ ጊዜ በላይ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የሚሰራበትን ሰርኩላር ኢኮኖሚ ስርዓት ኢትዮጵያ ልትተገብር መሆኑ ተነገረ

  • sheger1021fm
  • Oct 2
  • 1 min read
ree
ree

ስርዓቱ የአካባቢ ብክለትን በመከላከል የስራ እድል ፈጠራን የሚያበረታታና ለኢኮኖሚውም አስተዋጽኦ የሚያበረክት ነው ተብሏል፡፡


በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ የጀመረቻቸው ስራዎች መኖራቸው የተነገረ ሲሆን ለዚህም አንዱ ማሳያ ከየመኖሪያና ኢንደስትሪዎች የሚሰበሰቡ ቆሻሻዎችን ወደ ሀብት መቀየር ላይ አየተሰሩ ያሉትን የሚጠቅሱት የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተሯ ኢንጂነር  ሌሊሴ ነሜ ናቸው፡፡


ስርዓቱ በተለያዩ ሁኔታዎች በቀን ተቀን ህይወታችን የምንጠቀማቸውን ምርቶች የሚወጡ ቆሻሻዎች መልሰን መጠቀም የሚያስችል ሂደት ነው በተለይ በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች በግብርና በማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪ በምንጠቀማቸው እቃዎች መልሶ ማልማት  የምንችላቸውን እቃዎችን ማበረታታት ያካትታል ብለዋል።


የአሠራር ስርዓቱን በህግ አስደግፎ ለመተግበርም ኢትዮጵያ በቅርቡ የሰርኩላር ኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ ይፋ ማድረጓንና ይህም ከአካባቢ ጥበቃ አንፃር መልሰው ጥቅም የሚሰጡ ምርቶችና ከስነ ምህዳር ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ ለማድረግ ከግል ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያግዝ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሯ ጠቅሰዋል።


አንድ ሰው  በቀን እስከ ሁለት ኪሎ ግራም ቆሻሻ ከየመኖሪያ ቤቱ ያመነጫል የሚሉት ዋና ዳይሬክተሯ ሀገሪቱ ካላት የህዝብ ቁጥር አኳያ በእንዲህ አይነት መንገዶች መልሰው ጥቅም እንዲሰጡ ቢደረግ ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ በስራ እድል ፈጠራም አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።


ኢትዮጵያ ትናንት የአፍሪካ ሰርኩላር ኢኮኖሚ ወይም ኡደትን መሰረት ያደረገና ከአካባቢ ጋር የተጣጣሙና መልሰው ጥቅም ላይ የሚውሉ ምርቶች የሚተገበሩበት ፕሮግራም ይፋ አደርጋለች።


ዝግጁቱን የአካበቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከጂአይ ዜድ፣ኖውሬጂያን ቸርች ኤይድ፣አፍሪካን ሰርኩላር እና ሪች ፎር ጄንጅ ያሰናዱት ነው።


ስርዓቱ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንዲደረግም በተለይ ቆሻሻን መልሰው ጥቅም ላይ በማዋል የተሰማሩ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ለማበረታታት ስራው የሚጠይቀውን የፋይናንስ አቅርቦት ለማሟላት ከአለም አቀፍ ተቋማት ድጋፍ እንዲያገኙ ይደረጋል ተብሏል።


ምህረት ስዩም


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…

👇👇👇


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page