top of page

መስከረም 14 2018 - በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት ከሚያስተናግዱ አህጉራት አፍሪካ ቀዳሚዋ ናት

  • Sep 24, 2025
  • 1 min read

አህጉሪቱ ለአካባቢ ብክለት የምታበረክተው አስተዋፅኦ ግን ዝቅተኛ ነው ፡፡


በቅርቡ በተደረገው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ምክክር ከተደረጉባቸው ጉባኤዎች መካከል ለአየር ንብረት ለወጥ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ ማቅረብ የሚለው አንዱ ሲሆን አፍሪካ ከተደራዳሪነት ይልቅ መፍትሄ አቅራቢ እንድትሆን መስራት ይገባልም ተብሏል በጉባኤው፡፡


በዚህ ጉባኤ ከ200 ቢሊዮን ዶላር በላይ ፈንድ ቃልም ተገብቷል፡፡


የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የአካባቢና የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነትና ስትራቴጂክ አጋርነት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ መንሱር ደሴ አፍሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ ችግሮች የራሷን መፍትሄ እስካሁንም ድረስ ስትወስድ ነበር ብለዋል፡፡


በቅርቡም ኢትዮጵያ ባስተናገደችው የአህጉሪቱ የአየር ንብረት ጉባኤ የተለያዩ አፍሪካዊ መፍትሄዎች መቅረባቸውን ይጠቅሳሉ፡፡


አፍሪካ አሁን እየሰራች ያለው ለአየር ንብረት ለውጥ ተፈጥሯዊ መፍትሄ መስጠት ላይ ነው አለም ደግሞ ለዚህ ትኩረት አልሰጠም ይላሉ፡፡


አፍሪካ ውስጥ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ የሚሆን ማዕድን አለ ኢትዮጵያ ባካሄደችው የአህጉሪቱ የአየር ንብረት ጉባኤ እነዚህ ማዕድናት እዚሁ አፍሪካ ውስጥ ወደ ስራ መዋል የሚቻልበት ዙሪያም ምክክር ተደርጓል በማለት አቶ መንሱር ደሴ ያስረዳሉ፡፡


አለም ላይ ያለው የአየር ንብረት የፋይናንስ አካሄድ ትክክል አይደለም የሚሉት አቶ መንሱር ደሴ ይህም መስተካከል አለበት ሲሉ ይናገራሉ፡፡


በዚህ ዙሪያ የሚሰሩ እረጂ ተቋማትም ይሁን ሀገራት ከአፍሪካ ጋር አጋር በመሆን አብረው መስራት አለባቸው ይህ ከሆነ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የሚታይ መፍትሄ ማምጣት ይቻላል ባይ ናቸው፡፡


አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚደርስባት የጎርፍ ፣ ድርቅ ፣ ረሃብ እና ሌሎች ችግሮች እንዲያበቁ በትኩረት መስራት አለባት ተብሏል፡፡


በረከት አካሉ


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…👇👇👇👇👇👇


Recent Posts

See All
ከህዳሴ ግድብ ከ11 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ ዓሣ ተመረተ፡፡

ሐምሌ 21 2018 ከህዳሴ ግድብ ከ11 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ ዓሣ ተመረተ፡፡ የዓሣ ምርቱ ወደ መሃል ሃገር እየተጫነ ለአዲስ አበባ ገበያ እየቀረበ ነውም ተብሏል፡፡ ታላቁ የህዳሴ ግድብ መገንባቱን ተከትሎ በተፈጠረው ንጋት ሰው ሰራሽ ሃይቅ በኢትዮጵያ ትልቁና ከ70 በላይ ደሴቶች ያሉት የውሃ አካል ነው፡፡ ከቅርብ

 
 
 
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 30.65 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ የኃይል ማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ አደረገ።

ሐምሌ 20 2018 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 30.65 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ የኃይል ማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ አደረገ። እቅዱ የኔትወርክ ማሻሻያ እና ማስፋፊያ፣ የሰብስቴሽን እና ተያያዥ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች፣ ስማርት ግሪድ እና ቆጣሪ ማስፋፋትን እንደሚያካትት አገልግሎቱ ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page