top of page

መስከረም 13 2018 - ወጣቶች የራሳቸውን ስራ እንዳይፈጥሩ ፈተና የሚሆንባቸው ምንድነው?

  • sheger1021fm
  • Sep 23
  • 2 min read

መንግስት በየጊዜው ከት/ት ተቋማት ለሚመረቁ ሁሉ ስራ መስጠት ስለማይቻል ወጣቱ የራሱን የስራ እድል ይፍጠር ሲል ይሰማል፡፡


መንግስት ወጣቶችን በሚመለከት ከተቀጣሪነት ወደ ስራ ፈጣሪነት ተሸጋገሩ ቢልም በርካታ ወጣቶች የቢዝነሱ እና የፈጠራ ሃሳቡ ኖሯቸው ሀሳባቸውን መሬት ላይ ለማውረድ የገንዘብና መሰል ችግሮች እጃቸውን አጣጥፈው ተቀጣሪነትን ብቻ እንዲመርጡ እንዳደረጋቸው ይነገራል።


ለመሆኑ አሁን ላይ ወጣቱ የራሱን ስራ እንዲሰራ ወይም መንግስት እንደሚለው ስራ ፈጣሪ እንዲሆን ምን ዓይነት ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥሮለት ይሆን?


ወደ ስራው የገቡት ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎችስ ያሉባቸው ችግሮች ምንድን ናቸው? የኢትዮጵያ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች ማህበር አባላትን አነጋግረናል።


የማህበሩ አባልና ስራ ፈጣሪዋ ፎዚያ መሀመድ ከዓመታት በፊት በዘርፉ የነበሩ ችግሮች እየተቃለሉ የመጡ ቢሆንም አሁንም ግን ችግሮች ሙሉ በሙሉ አልተፈቱም ትላለች።


ለአብነት የገንዘብ ችግር፣ የገበያ ትስስር አለመኖር፣ እንዲሁም መንግስት ምርቶችን ሲገዛ ወይም ግዥ ሲፈፅም ከሀገር ውስጥ አምራቾች ይልቅ ቅድሚያ የሚሰጠው ለውጭ ድርጅቶች በመሆኑ የሀገር ውስጥ አምራቾች እንዳይበረታቱ አድርጓል ብላለች።


ሌላኛው የማህበሩ አባል ዳዊት ያዜ ለጀማሪ ስራ ፈጣሪዎችም ሆነ ወደ ዘርፉ ለሚቀላቀሉት የሚሰጠው ትኩረት ወይም ምቹ ሁኔታ ከባለፉት ዓመታት እየተሻሻሉ ቢሆንም ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሲነፃፀር ግን ለጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች እምብዛም ምቹ ሁኔታ እንዳልተፈጠረ ይናገራል።


ወጣቶቹ በዘርፉ ላይ አሁንም ችግር ሆነው ቀጥለዋል ከሚሏቸው ጉዳዮች መካከል የገንዘብ፣ የመስሪያ ቦታ(ሼድ) እና የገበያ ትስስር ችግር እንዲሁም በመንግስት መስሪያ ቤቶች ያለው የቢሮክራሲ አሰራር ይገኙበታል።


ለመሆኑ እነዚህን ችግሮች በተመለከተ የሚመለከተው መስሪያ ቤት ምን ይላል? የስራና ክህሎት ሚኒስቴርን ጠይቀናል።


በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የስራ ስምሪት ማስፋፊያ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ አሰፋ ፈረደ ለሁሉም ወጣቶች የስራ መከወኛ ገንዘብም ሆነ የመስሪያ ቦታ ለመስጠት መንግስት ብቻውን የማድረግ አቅም የለውም ይላሉ።


ሆኖም ግን ወጣቱ የራሱን ስራ እንዲጀምር ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ፖሊሲዎችን እያሻሻልን ነው ብለዋል።


ዘርፉ ላይ በርካታ ስራዎች ይጠይቃል ያሉት አቶ አሰፋ ችግሮችም ሙሉ በሙሉ ተፈተዋል ማለት አይቻልም ብለዋል።

ፍቅሩ አምባቸው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Recent Posts

See All
ጥቅምት 20 2018 - የፍትህ ስርዓት ችግር ምክንያት ስራው ላይ እክል እየገጠመው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ

የሚሰጣቸውን ምክረ ሃሳቦች ያለ በቂ ምክንያት የማይፈፅሙ ተቋማት በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ቢሞክርም ባለው የፍትህ ስርዓት ችግር ምክንያት ስራው ላይ እክል እየገጠመው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ፡፡ ተቋሙ የአስተዳደር በደል ደረሰብን እምባችን ይታበስልን የሚሉ አቤት ባዮችን ቅሬታ በመቀበል

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page