top of page

መስከረም 13 2018 - በኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ገበያው የሚፈልገውን የሰለጠነ በቂ የሰው ሀይል

  • sheger1021fm
  • Sep 23
  • 1 min read

በኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ገበያው የሚፈልገውን የሰለጠነ በቂ የሰው ሀይል ማግኘት ከባድ መሆኑ ይነገራል።


በቴክኖሎጂው ዘርፍ ባለሞያዎች ሲፈለጉ ብዙ ጊዜ ከተለያዩ ሀገራት እየመጡ እንደሚቀጠሩም ሲነገር ይሰማል።


በዘርፉ ያለውን የባለሞያ እጥረት እቀርፋለሁ፣ ወጣቶችም በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ እሰራለሁ ያለ በአሜሪካን ሀገር ሲሰራ የቆየ ተቋም በኢትዮጵያ ቅርንጫፉን ከፍቷል።


ላለፉት 13 ዓመታት በአሜሪካን ሀገር የኮምፒውተር እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስልጠና በመስጠት ሲሰራ የቆየው ቤማንዳ ሶሉሽን አሁን በኢትዮጵያ ቅርንጫፍ መክፈቱን ተናግሯል።


በአጫር ስልጠና በገበያው ያለውን ፍላጎት መሙላት ቀዳሚው ስራዬ ይሆናል ሲልም ተናግሯል።


ተቋሙ በአሜሪካን ሀገር በተለይም እንደ ሜሪላንድ፣ ቨርጂኒያና ዲሲ ባሉት አካባቢዎች ያሉ ኢትዮጵያዊያንን አስተምሮ የተሻለ ስራ ላይ እንዲሰማሩ በማድረጉ ይታወቃል ተብሏል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page