top of page

መስከረም 12 2018 የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በሸገር ሬዲዮ ጋዜጠኛ ትዕግስት ዘሪሁን እና ምንታምር ፀጋው የምርመራ መዝገብ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለመስከረም 14 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጠ፡፡

  • sheger1021fm
  • Sep 22
  • 1 min read
ree

የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ፣ ጋዜጠኞቹን በቁጥጥሩ ስር ካደረገ በኋላ ለ2ኛ ጊዜ ተጨማሪ የምርመራ ቀጠሮ እንዲሰጠው ቢያመለክትም ጉዳዩን ያየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በ50 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ መስከረም 7/2018 ዓ.ም ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወሳል፡፡


በውሳኔው ቅር የተሰኘው ፖሊስ በይግባኝ ለጠቅላይ ፍ/ቤት አመልክቷል፡፡


የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት 2ኛ የወንጀል ይግባኝ  ችሎት ፣ ዛሬ በዋለው ችሎቱ ፣ የፌዴራል ፖሊስና የጋዜጠኞቹን ጠበቃ አቤቱታ ካዳመጠ በኋላ ውሳኔ ለመስጠት ለመስከረም 14 ቀን 2018 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡


የሸገር ሬዲዮ ጋዜጠኞች ትዕግስት ዘሪሁን እና ምንታምር ፀጋው በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቁጥጥር ስር ከዋሉ ዛሬ 20ኛ ቀናቸው ነው፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




 
 
 
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page