ሐምሌ 7 2017 - አባይ ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ያልተጣራ 4.3 ቢሊዮን ብር አተረፍኩ አለ
- sheger1021fm
- Jul 14
- 1 min read

ይህም ከ2016 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ120 በመቶ ብልጫ አለው ሲል ዛሬ በሰጠው መግለጫ ተናግሯል።
ጠቅላላ የባንኩ ገቢ ደግሞ 16.2 ቢሊዮን ሲሆን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከርም የ95 በመቶ እድገት አሳይቷል ተብሏል።
ባንኩ ይህንን ያለው 15ተኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ባለበት ወቅት ነው።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ባንኩ የተቀማጭ ገንዝብ መጠኑን ከባለፈው ዓመት በ37 በመቶ በማሳደግ 72 ቢሊዮን ብር ያደረሰ ሲሆን ጠቅላላ ሐብቱም የ38 በመቶ እድገት በማስመዝገብ 93 ቢሊዮን ብር ሆኗል ተብሏል።
አባይ ባንክ ለተለያየ የኢኮኖሚ ዘርፍ የሰጠው ጠቅላላ ብድር 47.5 ቢሊዮን ብር መድረሱን የተናገሩት ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ የኋላ ገሠሠ ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢውን የ95 በመቶ እድገት በማሳየት 16.2 ቢሊዮን ማድረሱን ተናግረዋል።
የባንኩ ቅርንጫፎችም ከ555 በላይ ሲሆን የዲጂታል ባንከ አገልግሎት አማራጮችን በማቅረብ የደንበኞችን ቁጥር ከ4 ሚሊዮን በላይ ማድረሱን ተናግሯል።
በተጨማሪም አባይ ባን 15ተኛ አመት የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከዛሬ ሐምሌ 7 ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ዝግጅቶች አከብራለሁ ብሏል።
ለወራት በሚቆየው ዝግጅትም የችግኝ ተከላ፣ የደም ልገሳ እንዲሁም የማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓትን ያካተተ መረሀ ግብር ይኖረኛል ያለው ባንኩ ለአንድ ሳምንት ደግሞ የደንበኞች ቀንን እንደሚያከብር ተናግሯል።
አባይ ባንክ በ823 መሰራች ባለአክሲዮኖች 125.8 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል ሥራ የጀመረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የባለአክሲዮኖችን ቁጥሩ 4,500 ፣ የተከፈለ ካፒታሉን ደግሞ 7 ቢሊዮን ብር ማድረሱን ሰምተናል ተነግሮለታል።
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.cocxjmm3s








