ሐምሌ 5 2017 - አሽሊ ፈርኒቸር ምርቶቹን በኢትዮጵያ ገበያ መሸጥ ሊጀምር ነው
- sheger1021fm
- Jul 12
- 1 min read
የአሜሪካው አሽሊ ፈርኒቸር ምርቶቹን በኢትዮጵያ ገበያ መሸጥ ሊጀምር ነው።
ለዚህም ሲባል አሽሊ ፈርኒቸር ከሀገር ቤቱ ዩስራ ሆም ጋር ስምምነት አስሯል።
የስምምነት ፊርማው ትናንት ምሽት በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ውስጥ በሚገኘው ፖላስ ኮርት ተፈርሟል።
የአሜሪካ አምባሳደር ኢርቪን ማሲንጋ፣ ዲፕሎማቶች፣ የቢዝነስ አቀላጣፊዎችና ሌሎችም በፊርማ ስነ ስርዓቱ ወቅት ተገኝተዋል።

በዩስራ ሆምስ በኩል በኢትዮጵያ ምርቶቹን በቀጥታ መሸጥ የሚጀምረው አሽሊ ፈርኒቸር ኢንዱስትሪዎች በዓለም ላይ ትልቁ የቤት ዕቃዎች አምራች መሆኑ ይነገርለታል፡፡
ከዩስራ ሆም ጋር በተደረገው ልዩ አጋርነት አሽሊ ፈርኒቸር ወደ ኢትዮጵያ ገበያ በመግባት የቤት እቃዎችን በቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ አስገብቶ እንዲሸጥ ያስችለዋል ተብሏል፡፡
የአሽሊ የፈርኒቸር ምርቶችን በኢትዮጵያ ገበያ ለማምጣት ስመምነት ያሰረው ዩስራ ሆምስ በፈርኒቸር ዘርፍ የ5 ዓመት ልምድ እንዳለው ሲናገር ሰምተናል።
አሽሊ ፈርኒቸር ከ125 በላይ ሀገራት ከ1,125 በላይ የምርት ማሳያዎች( showrooms) አሉት ተብሏል።
በአፍሪካም በኬንያ፣ ዛመቢያ፣ ሊቢያ፣ ሞሪሺየስ አንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ምርቶቹን ይሸጣል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
Comments