top of page

ሐምሌ 28 2017 - የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አባል የሆኑበት የአፍሪካ ቢዝነስ ስኩል ማህበር፤ በመጪው ዓመት ዓመታዊ ኮንፈረንሱን በኢትዮጵያ ያካሄዳል ተባለ፡፡

  • sheger1021fm
  • Aug 4
  • 2 min read

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አባል የሆኑበት የአፍሪካ ቢዝነስ ስኩል ማህበር፤ በመጪው ዓመት ዓመታዊ ኮንፈረንሱን በኢትዮጵያ ያካሄዳል ተባለ፡፡


ኮንፈረንሱ የሚካሄደው የአፍሪካ ቢዝነስ ስኩል ማህበር ከክቡር ኮሌጅ ጋር በጋራ መሆኑን ሰምተናል፡፡


በዚህም በ2018 ዓ.ም የሚያሰናዳውን ዓመታዊ ኮንፈረንስ ኢትዮጵያ እንድታዘጋጅ ተመርጣለች የተባለ ሲሆን ዝግጅቱ በመጪው ዓመት ከግንቦት 12 እስከ 14 ቀን በአዲስ አበባ ይካሄዳል ተብሏል፡፡


ይህን የሰማነው የአፍሪካ ንግድ ትምህርት ቤቶች ማህበር ከክቡር ኮሌጅ ጋር በመሆን በተሰጡት መግለጫ ላይ ነው፡፡


በኮንፈረንሱ ከ150 በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ዳይሬክተሮች እና የአለም አቀፍ አካዳሚክ መሪዎች ከመላው አፍሪካ እና ከዓለም አቀፍ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡


ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ክቡር ኮሌጅ በማህበሩ ብቸኛ አባል ነው ተብሏል፡፡

ree

ኮሌጁ ከ2 ዓመት በፊት የሚጠበቅበትን መስፈርት አሟልቶ ያቀረበዉ ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ የ2026 የማህበሩ ዓመታዊ ጉባኤ በክቡር ኮሌጅ አዘጋጅነት ኢትዮጵያ እንድታካሄድ መመረጧን የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ገበየሁ ተናግረዋል፡፡


የአፍሪካ ቢዝነስ ስኩል ማህበር በ2018 ዓ.ም በወርሀ ግንቦት በኢትዮጵያ በሚያሰናዳው መርሃ ግብር ከትምህርት ሚኒስቴር፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በጋራ በመሆን ነው ተብሏል፡፡


እንዲህ አይነት ኮንፈረንስም በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ/አለም አቀፍ ተቋማት መካከል የእውቀት ሽግግር እንዲኖር፣ በምርምር፣ በፈጠራ፣ በፋኩልቲ ልማት እና በስራ ፈጠራ ውስጥ ስትራቴጂካዊ አጋርነት እንዲፈጠር ያደርጋል ያሉት አቶ ተፈራ በተጨማሪም የኢትዮጵያን የንግድ ተቋማት ከከፍተኛ ትምህረት ተቋማት ጋር በጋራ የሚሰሩበትን አጋጣሚ መፍጠርን ጨምሮ የኮንፍረስ ቱሪዝም ተጠቃሚነት እንዲያድግ ያደርጋል ተብሎ ተስፋ እንደተጣለበት ተናግረዋል፡፡


ክቡር ኮሌጅ ላለፉት 20 ዓመታት በትምህርት ስራ ውስጥ የቆየ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ላለፉት 4 ዓመታት ደግሞ የኮሌጅ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ተብሏል፡፡


የትምህርት ጥራትን ከማሻሻል አንፃር በአፍሪካ ውስጥ ካሉ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ልምድ ለመውሰድ የሚያግዘው አንደኛው መንገድ የአፍሪካ ቢዝነስ ስኩል ማህበር አባል መሆን ነው ያሉት ደግሞ የኮሌጁ ስራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ መኩሪያ በዚህም ክቡር ኮሌጅ ወደ ስራ ከገባበት ዓመት ጀምሮ በማህበሩ መታቀፉን ተናግረዋል፡፡

ree

ከዚሁ ወሬ ጋር በተያያዘ ክቡር ኮሌጅ በመጀመሪያ ዲግሪ እና በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ያስተማራቸውን 72 ተማሪዎች ሰሞኑን አስመርቋል።


በዕለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት የአፍሪካ ቢዝነስ ስኩል ማህበር ዳይሬክተር ላና ኤልራምሊ ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።


እንዲሁም በዕለቱ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተመራቂዎች ሜዳሊያና የዋንጫ ሸልማት ተበርክቶለታል።


ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page