ሐምሌ 28 2017 - የተቀማጭ ገንዘብ መድህን ፈንድ በተቀመጠው መሰረት የቆጣቢዎችን ገንዘብ መመልስ ችሎ ይሆን?
- sheger1021fm
- Aug 4
- 1 min read
ባንኮችና የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት በተለያየ ምክንያት ከስረው ከገበያ ቢወጡ፣ ለቆጣቢዎች ዋስትና እሰጣለሁ፣ በፋይናንስ ተቋሙ ያስቀመጡትን ገንዘብ እመልስላቸዋለው ብሎ ስራ የጀመረው የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድህን ፈንድ በተቋቋመ በአጭር ጊዜ ውስጥ በተግባር ተፈትኗል።
በመድህን ፈንዱ አሰራር መሰረት የፋይናንስ ተቋም ከስሮ ቢዘጋ ከ100,000 ብር በታች ተቀማጭ ያላቸው የባንክ ደንበኞች ሙሉ ገንዘባቸውን ከ90 ቀን ባነሰ ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ያገኛሉ።
በቅርብ ጊዜ ውስጥ አንድ ማይክሮ ፍይናንስ ተቋም ከስሮ ከገበያ ስለመውጣቱ ተሰምቷል፡፡
በመጠንና አቅሙ አነስተኛ ነው የተባለው የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ውስጥ የቁጠባ ሂሳብ ያላቸው ሰዎች ብዙ አለመሆናቸው ቢነገርም አዲስ ለተቋቋመው የመድህን ፈንድ ግን አጋጣሚው በተግባር የሚፈተንበት ሆኗል።
በአሰራሩ በተቀመጠው መሰረት የቆጣቢዎችን ገንዘብ መመልስ ችሎ ይሆን? ይህን ለማድረግስ ምን ያህል ጊዜ ይወስድበታል?
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ……
ቴዎድሮስ ወርቁ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s











Comments