top of page

ሐምሌ 27፣2016 - ባንኮች ከሚገዙበትና ከሚሸጡበት ይፋዊ የምንዛሬ ዋጋ ውጭ በተጨማሪነት ኮሚሽን እና ሌሎች ክፍያዎችን ለብቻ ማስከፈል እንዲያቆሙ ተወሰነ፡፡

  • Aug 3, 2024
  • 1 min read

#የኢትዮጵያ_ብሔራዊ_ባንክ_የዳይሬክተሮች ቦርድ ባንኮች ይፋ ከሚያደርጉት የውጭ ምንዛሬ መግዣና መሸጫ ዋጋ ውጭ የሚያስከፍሉትን ኮሚሽን እና ሌላ ክፍያ እንዲያቆሙ መወሰኑ ተሰምቷል፡፡


እንዲህ ያሉ ክፍያዎችን ካስከፈሉ እንኳን ከመግዣና መሸጫ ዋጋው ጋር አካተው አንድ ላይ ለደንበኞቻቸው ይፋ እንዲያደርጉት መወሰኑን ከብሔራዊ ባንክ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡


ይህም #የውጭ_ምንዛሬ ግዥና ሽያጭ ላይ ግልፅነትን ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል፡፡


ስለ ጉዳዩ ሸገር የጠየቃቸው የምጣኔ ሐብት ባለሙያ ውሳኔው ለባንክ ደንበኞች የሚበጅ ነው ብለዋል፡፡


ይህን ሲያስረዱም የአንዳንድ ምግብ ቤቶችን የዋጋ ዝርዝር እንደ ምሳሌ ያነሳሉ፡፡


ሂሳብ ሲያስከፍሉ የምግብ መዘርዘሩ ላይ ከተቀመጠው ዋጋ በላይ የሚጠይቁ አሉ ለዚህም ምክንያቱን ሲጠየቁ የምግብ መዘርዝሩ ላይ የሰፈረው ዋጋ ቫትን አይጨምርም ይላሉ፡፡


ይህ ለደንበኞች ግልፅነት የጎደለው ወይም መጀመሪያውኑ አጠቃላይ ዋጋውን አይተው እንዳይወስኑ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡


አሁን ባንኮች የውጭ ምንዛሬ ሲሸጡና ሲገዙ የሚያስከፍሉት ኮሚሽን እና ሌላ በፐርሰንት የሚሰላ ክፍያ ካለ ይፍ በሚያደርጉት የመግዣና መሸጫ ላይ እንዲያካትቱ መወሰኑም ደንበኞች ይፋ ከተደረገው ዋጋ ሌላ ክፍያ ስለማይጠይቁ አሰራሩን ግልፅ ያደርገዋል ብለዋል ባለሞያው፡፡


በሌላ በኩል ግን ይህ አሰራር ደንበኞች ከውጭ ግዢ ለመፈፀም LC ለመክፈት ሲጠይቁ የሚኖረውን ግብይት አይመለከትም ተብሏል፡፡


ውሳኔው ከዛሬ ጀምሮ ስራ ላይ መዋል መጀመሩንም ብሔራዊ ባንክ እወቁልኝ ብሏል፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን

Recent Posts

See All
ዘንድሮ በአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተና ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች 66 በመቶዎቹ ተማሪዎቻቸው ሙሉ በሙሉ የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡

ሰኔ 22/2018 ዘንድሮ በአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተና ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች 66 በመቶዎቹ ተማሪዎቻቸው ሙሉ በሙሉ የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡ የከተማዋ ትምህርት ቢሮ በሰጠው መግለጫ ከመንግስት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች 95 ነጥብ 8 በመቶ፤ ከግል ት/ቤት ተማሪዎች ደግሞ ከ99

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page