top of page

ሐምሌ 26፣2016 - በግለሰብ ሱቅ ውስጥ የተከማቸ ነዳጅ ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል

  • Aug 2, 2024
  • 1 min read

ትናንት በተከሰተ የእሳት አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡


አደጋው የተከሰተው ትናንት ሀምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ቡልቡላ ማርያም ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ነው፡፡


#የእሳት_አደጋዉ የተከሰተዉ በአንድ የመኪና ዕቃ መለዋወጫ ሱቅ ዉስጥ ሲሆን በሱቁ ተቀጥራ የምትሰራ የ20 ዓመት ወጣት በእሳት አደጋዉ ህይወቷ ወዲያው ማለፉ ተነግሯል።


በተጨማሪ ሁለት ሰዎች በጭስ የመታፈን ጉዳት እንደደረሰባቸው የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን ለሸገር ተናግሯል፡፡


የእሳት አደጋ ተስፋፍቶ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር እንደተቻለ በባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ ንጋቱ ማሞ ነግረውናል፡፡


#ነዳጅ መከማቸት ያለበት በነዳጅ ማደያዎች መሆን ሲገባው በየግለሰብ ቤቶችና ሱቆች እየተከማቸ መሆኑ የእሳት አደጋ ሲከሰት የማባባስ አቅም ይኖራቸዋል የሚሉት ባለሙያው፣

በተከሰተው አደጋ ተከማችቶ የነበረው ነዳጅ ቃጠሎውን ያባባሰው በመሆኑ ተጎጂዋ እራሷን ማትረፍ እንዳትችል እንዳደረጋት ጠቁመዋል፡፡


ቃጠሎው የደረሰበት  የመለዋወጫ ሱቅ ሙሉ በሙሉ በእሳቱ ወድሟል፤ መጠኑ ያልታወቀ ንብረት መውደሙንም ከላፊው ሰምተናል፡፡


ምንታምር ፀጋው

Recent Posts

See All
የመንግስት ግዥ አገልግሎት በዘንድሮው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ንብረቶች የተገኘ ወደ 323 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ አድርጌያለሁ አለ፡፡

ግንቦት 17/2018 የመንግስት ግዥ አገልግሎት በዘንድሮው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ንብረቶች የተገኘ ወደ 323 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ አድርጌያለሁ አለ፡፡ አገልግሎቱ ይህን ያህል ገንዘብ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ለመንግስት ገቢ ሲያደርግ በታሪኩ የአሁኑ የጀመ

 
 
 

1 Comment


lemmatesfaye99
Aug 03, 2024

መሰገብገብ ለዚህ ይዳርጋል ገነናለገና አባት ለመሰብሰብ ተብሎ የሰው ሕይወት መጥፋት የለበት

Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page