ሐምሌ 25 2017 - አቤቱታ የቀረበበትን የምክር ቤት ወንበር ድልድልን የተመለከተውን ህግ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማፅደቁ ተነገረ
- sheger1021fm
- Aug 1
- 1 min read
ከዚህ ቀደም ለህገ መንግስት አጣሪ ጉባኤ አቤቱታ የቀረበበትን የምክር ቤት ወንበር ድልድልን የተመለከተውን ህግ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማፅደቁ ተነገረ፡፡
ያለ አዋጅ ማሻሻያ ተደርጎበት የጸደቀው የክልሉ ምክር ቤት የወንበር ቁጥር ቀድሞ ከነበረበት 99 ወደ 165 ያደገው መቀመጫ እንደ አዲስ የሚዋቀረውን ለተቀሩት የምርጫ ክልሎች የሚከፋፈል ነው ተብሏል፡፡
ክልሉ ከዚህ ቀደም በአዋጅ ያፀደቀውን የምርጫ ክልል አወቃቀር የሚያስቀረውን ይህንን ውሳኔ ያሳለፈው የአዋጅ ማሻሻያ ሳያደርግ ቃል በቀረበ ገለፃ ላይ ተመስርቶ ነበርም ተብሏል፡፡
የክልሉ ምክር ቤት የመቀመጫ ቁጥሩን ለማሳደግ ያቀረበውን ማሻሻያ ተከትሎ የቦሮ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የምክር ቤት አባላት በወቅቱ ሀሳቡን በመቃወማቸው ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ ለእስር መደረጋቸውን ፓርቲው መናገሩ ይታወሳል፡፡
ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አቤቱታ ያቀረበበትን የምርጫ ክልሎችን በአዲስ መልክ ለማዋቀር የአዋጅ ማሻሻያ ተደረገበትን ውሳኔ ተከትሎ የቦሮ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምን ይላል? የሚለውን ሀሳብ ለመቀበል የፓርቲው ፕሬዝዳንት ጋር ደጋግመን ብንደውል ልናገኛቸው አልቻልንም፡፡
ፓርቲው በወቅቱ በማሻሻያ ዙሪያ ያነሳው ቅሬታ እና ተቃውሞ በተለይም ውክልና ያገኘሁበትን የመተከል ዞን የመቀመጫ ቁጥርን ጥያቄ ውስጥ የሚጥልብኝ ነው በሚል መሆኑ ይታወሳል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://www.mixcloud.com/ShegerFM/653456/
የኔነህ ሲሳይ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s











Comments