ሐምሌ 25 2017 - ቡና ባንክ በማንኛውም አይነት ሞባይል ስልክ እንዲሁም ያለኢንተርኔትም የነዳጅ ክፍያ የሚከወንበት ስርዓት አስተዋወቀ
- sheger1021fm
- Aug 2
- 1 min read
ቡና ባንክ በማንኛውም አይነት ሞባይል ስልክ እንዲሁም ያለኢንተርኔትም የነዳጅ ክፍያ የሚከወንበት ስርዓት አስተዋወቀ፡፡
ባንኩ የዲጂታል ክፍያ ስርዓቱን ያስጀመረው ከትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ነው ተብሏል፡፡
ቡና ባንክ ዛሬ በይፋ ያስተዋወቀው የክፍያ ስርዓት፤ በተለይ በነዳጅ ማደያዎች ውስጥ የሚስተዋሉ ረጃጅም ወረፋዎችን በመቀነሱ የራሱ የሆነ አስተዋጽዖ እንደሚያደርግም ተነግሮለታል፡፡

የቡና ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ታፈሰወርቅ ንጉሴ፤ እስካሁን 12 ሚሊዮን ብር ገደማ በዚህ ስርዓት አገበያይተናል ብለዋል፡፡
የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ቡና ባንክን ተጠቅመዉ የነዳጅ ግዢን መፈጸም የሚችሉት፤ ከነዳጅ ማደያዉ *820# በመጠቀም ስልካቸዉ ላይ በሚደርሳቸዉ የማረጋገጫ መልዕክት፣ ‘’አቦል የሞባይል ባንኪንግ’’ መተግበሪያ ዉስጥ በመግባት ከውአር (QR) ኮድን ተጠቅሞ ስካን በማድረግ ወይም በነዳጅ ማደያው የቀረበውን የማጣቀሻ ቁጥር (Reference Number system) በመጠቀም መሆኑም ባንኩ አስረድቷል።

ቡና ባንክ ከደም ብሎ የጀመረው እንዲሁም ዛሬ በይፋ ያስተዋወቀው ይህ ክፍያ የሚከወንበት ስርዓት፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለትን ግልፅነት እና ቅልጥፍና ለማሻሻል አንዱ አማራጭ እንደሆነም የተናገሩት፤ በትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር የብሄራዊ የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ፕሮጀክት አስተባባሪ ሰልማን መሀመድ ናቸው፡፡
አሀን ላይ ባንኩ በተወሰኑ የተመረጡ የነዳጅ ማደያዎች የጀመረውን ይህን አገልግሎት በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ለማስፋት አቅጃለሁም ብሏል፡፡
ቡና ባንክ ከተቋቋመ 15 ዓመታት ማስቆጠሩ፣ የባለአከሲዮኖቹ ብዛት 13,000 መሆናቸውን እንዲሁም የቅርንጫፎቹ ብዛት 456 መደረሱ ተነግሯል፡፡
ማንያዘዋል ጌታሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s











Comments