ሐምሌ 25 2017 - ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ ወደ ቦታው እንዲመለስ፣ ወደ መቀሌ ካቀኑት የምክክር ኮሚሽነሮች ጋር የተወያዩ አካላት መጠየቃቸው ተነገረ
- sheger1021fm
- Aug 1
- 1 min read
ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ ወደ ቦታው እንዲመለስ፣ በሃይል የተያዙ አካባቢዎች እንዲለቀቁ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እና ሕወሐትን ጨምሮ ወደ መቀሌ ካቀኑት የምክክር ኮሚሽነሮች ጋር የተወያዩ አካላት መጠየቃቸው ተነገረ፡፡
ለኮሚሽነሮቹ ይህ ጥያቄ የቀረበው በትግራይ ምክክር ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታ እንዲፈጠር ወደ መቀሌ አቅንተው ከባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት ባካሄዱበት ወቅት ነው፡፡
የሀገራዊ ምክከር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ፣ ከህወሓት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ከተለያዩ አካላት ጋር ወይይት ማካሄዱን ተናግሯል፡፡
በውይይቱም ሁሉም አካላት በሁሉ መድረኮች ለምክር አስቻይ ሁኔታ እንዲፈጠር ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቄያቸው መመለስ እንዳለባቸው ፣ በሃይል የተያዙ መሬቶች እንዲለቀቁ ፣ ህገ መንግስታዊ ሥርዓት ወደ ቀድሞው ቦታ መመለስ አለበት የሚል ሀሳብ ማቅረባቸውን የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ ነግረውናል፡፡

በምክክሩ አስፈላጊነት ላይ ሁሉም የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደሚስማሙ የተናገረው ኮሚሽኑ ነገር ግን ከአገር አቀፉ ምክክር በፊት በክልሉ ውስጥ ምክር ያስፈልጋል የሚል እምነት እንዳላቻው ጠቁሟል፡፡
አሁን በክልሉ ያለው ሁኔታ ልክ በሌሎች ክልሎች የተካሄደውን ዓይነት ምክከር ለማካሄድ ይፈቅዳል የሚል እምነት እንደሌላቸው የውይይቱ ተሳታፊዎች መናገራቸውን አቶ ጥበቡ ታደሰ አስረድተዋል፡፡
መግባበት ካልተፈጠረ ትግራይን ዳግም ጦርነት ሊያገኛት ይችላል የሚል ስጋት በተለይ በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ስጋት መኖሩን ግዜያዊ አስተዳደሩን እና የሲቪል ማህበራትን ጭምሮ የውይይቱ ተሳታፊዎች መናገራቸውን ከኮሚሽኑ ሰምተናል፡፡
በመቀሌ ከተማ ከተደረጉ ወይይቶች ላይ በርካታ ግብአቶች ማግኘቱን የተናገረው የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኮሚሽኑ ስልጣን የሚፈቱ ችግሮችን መፍትሄ እንደሚሰጥ ተናግሮ የቀረቡ አንዳንድ ሀሳቦች ግን በኮሚሽኑ ስልጣን የሚፈቱ እንዳልሆኑ አስርድቷል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ...
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments