top of page

ሐምሌ 22 2017 - የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢትዮጵያን ጨምሮ ወደ ሀገራቸው ምርቶቻቸውን በሚልኩ 100 ሀገራት ላይ ለጣሉት ታሪፍ

  • sheger1021fm
  • Jul 29
  • 2 min read

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢትዮጵያን ጨምሮ ወደ ሀገራቸው ምርቶቻቸውን በሚልኩ 100 ሀገራት ላይ ለጣሉት ታሪፍ የንግድ ሚዛን ጉድለትን እንደ ምክንያት ማቅረባቸው ይታወሳል።


እነዚህ ሀገራት ከአሜሪካ ከሚገዙት ይልቅ ወደ አሜሪካ የሚልኩት ምርት ይበልጣል የሚል ምክንያት ሰጥተዋል።


አንድ የምጣኔ ሃብት ባለሞያ ግን ይህ ምክንያት ኢትዮጵያን አይመለከትም፤ ውሳኔውን ለማስቀየርም መረጃን መሰረት ያደረገ ውይይት ከአሜሪካ ጋር መቀመጥ ያስፈልጋል ብለዋል።

ree

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢትዮጵያን ጨምሮ ወደ ሀገራቸው ምርቶቻቸውን በሚልኩ 100 ሀገራት ላይ ታሪፍ ጥለዋል።


በኢትዮጵያ ላይ የተጣለው የ10 በመቶ ታሪፍ ነው።


ትራምፕ በሀገራቱ ላይ ታሪፉን የጣልኩት ከአሜሪካ ጋር ያላቸው የንግድ ሚዛን የተዛባ ስለሆነ ነው የሚል ምክንያት ሰጥተዋል።


ሀገራቱ ከአሜሪካ ከሚያስገቡት ይልቅ የሚልኩት ስለሚበልጥ የንግድ ሚዛን መዛባት ተፈጥሯል ብለዋል።

ታሪፉን ለመጣል የሰጡት ምክንያት አሳማኝ እንዳልሆነ የምጣኔ ሃብት ባለሞያው ዶክተር ታደለ ፈረደ ተናግረዋል።


በንግድ ልውውጡ እንዲያውም ተጎጂዋ ኢትዮጵያ ነች ብለዋል።


ትራምፕ በኢትዮጵያ ላይ የጣሉት የ10 በመቶ ታሪፍ በሁሉም ሀገራት ላይ የተጣለው የመነሻ ታሪፍ ወይም baseline tariff እንደሆነ ተነግሯል።


ይህም ከሌሎች ሀገራት አንጻር አነስተኛ ነው ሊባል እንደሚችል የሚጠቅሱት ዶክተር ታደለ ውሎ አድሮ ግን ጫና ማስከተሉ እንደማይቀር ተናግረዋል፡፡


በተለይ ወደ አሜሪካ የሚላኩ ቡና እና የጨርቃ ጨርቅ ምርቶች ሊጎዱ ይችላሉ ብለዋል፡፡


ኢትዮጵያ በአሜሪካ የተጣለባት የ10 በመቶ ታሪፍ እንዲቀርላት ምን ማሳመኛ ልታቀርብ ትችላለች ያልናቸው ዶክተር ታደለ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተውናል፡፡


አሜሪካ ከሰሃራ በስተደቡብ የሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ምርቶቻቸውን ከቀረጥ እና ኮታ ነጻ ወደ ሀገሯ እንዲያስገቡ ከሰጠችው ዕድል ኢትዮጵያ መታገዷም ይታወሳል።


ከአሜሪካ ጋር ውይይቱን ማካሄድ ከተቻለ ይህንንም ጉዳይ ማንሳት ይገባል ሲሉ የምጣኔ ሃብት ባለሞያው ዶክተር ታደለ ተናግረዋል።


ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ከምትልካቸው 92 በመቶውን የሚሸፍኑት አስር የምርት አይነቶች መሆናቸው ተጠቅሷል።


እነዚህ ምርቶች በዋናነት የሚላኩት ወደ እስያ እና አውሮፓ ገበያዎች እንደሆነም ጥናቱ ያመለክታል።

ወደ አሜሪካ የሚላኩት ስምንት በመቶዎቹ ብቻ እንደሆኑ በዚሁ ዙሪያ ጥናት ካካሄዱ ሞያተኞች አንዱ የሆኑት ዶክተር ታደለ ነግረውናል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….


ተያያዥ ዘገባቦችን ያድምጡ… (1) https://shorturl.at/ZKOH6



ንጋቱ ረጋሣ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page