top of page

ሐምሌ 22 2017 - በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 60 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች ጤንነቱ ባልተጠበቀ መልኩ ጽንስ እንደሚያቋርጡ ተነገረ

  • sheger1021fm
  • Jul 29, 2025
  • 1 min read

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 60 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች ጤንነቱ ባልተጠበቀ መልኩ ጽንስ እንደሚያቋርጡ ተነገረ፡፡


ወጣት ሴቶች ከገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍል ወደ ክልሉ ከተሞች ለስራ ብለው የሚመጡ እንዳሉ እና በዚህም ላልተፈለገ እርግዝና እንደሚጋለጡ ከክልሉ ጤና ቢሮ ሰምተናል፡፡


በዚህም በወር ከ1,000 በላይ የሆኑ ሴቶች ጽንስ እንደሚያቋርጡ ተነግሯል፡፡


ጽንስን በጤናማ መንገድና በተፈቀደው መሰረት በጤና ተቋማት የሚያቋርጡ ቢኖሩም ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት በቤታቸው እና ጤንነቱ ባልተጠበቀ መልኩ የሚያቋርጡ እንዳሉ ሰምተናል።

በአጠቃላይ በክልሉ በህግ በተፈቀደ እና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ጽንሰን የሚያቋርጡ አርባ በመቶ ብቻ እንደሆኑ የነገሩን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ውስጥ የቤተሰብ ዕቅድ እና የአፍላ ወጣቶች ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት አቶ ወንድሙ ናቸው፡፡


በክልሉ ከ32 በላይ ብሄረሰቦች የሚኖሩበትን እንደመሆኑ ጤንነቱ በተጠበቀ መልኩ ጽንስን ማቋረጥ የሚያውቁ እንዳሉ ሁሉ መረጃው ደግሞ ፍጹም የሌላቸው እንዳሉም አቶ ወንድሙ ነግረውናል፡፡


ኢትዮጵያ በ2030 የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ቃል መግባቷንና አስር በመቶ የሚሆኑት በዚህ ጽንስ በማቋረጥ እንደሚሞቱ የነገሩን በጤና ሚኒስቴር የሚኒስትር ዴኤታው ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ፕ/ር ስለሺ ጋሩማ ናቸው፡፡


ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page