ሐምሌ 2 2017 - የቱሪዝም ሚንስቴር Visit Ethiopia የተሰኘ ድረ ገፅ ይፋ አደረገ
- sheger1021fm
- Jul 9
- 1 min read
የቱሪዝም ሚንስቴር ቪዚት ኢትዮጵያ ( #Visit_Ethiopia ) የተሰኘ ድረ ገፅ ወይም ዌብሳይት ይፋ አደረገ።
ድረ ገፁ ቱሪስቶች ሀገሪቱ ውስጥ ያለው የቱሪዝም መዳረሻዎች መረጃ እንዲያውቁና የሆቴል፣ የአስጎብኚ ባለሙያዎች የቱሪዝም ቁሳቁስ ገበያዎችና ሌሎችም መረጃዎች እንዲያውቁ፣ ግብይት እንዲፈፅሙ ያደርጋል ተብሏል።
ድረ ገፁን የመረጃ መረብ ደህንነት አስተዳደር ከቱሪዝም ሚንስቴር ጋር በመሆን አልምቶታል የተባለ ሲሆን ቱሪዝምን ዲጅታል የማድረግና ዘርፉን ለማሳደግ እየተሰራ ላለው ስራ አንዱ ማሳያ ነው ሲሉ የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ ተናግረዋል።
ድረ ገፁ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ ይመጣልም ተብሏል።
ቱሪስቶች ወደ አንድ መዳረሻ ከመሄዳቸው በፊት ስለ ስፍራው በቂ መረጃን ይፈልጋሉ፣ ስፍራውን ከጎበኙ በኋላም የተሰማቸውን ሃሳብ ማካፈል ይወዳሉ ይህ መተግበሪያም እነዚህ ጉዳዮችን በተገቢው መንገድ ይዟል ብለዋል።

ተጓዦች አንዱ ቦታ ከጎበኙ በኋላ በድረ ገፅ ሃሳባቸውን ማካፈል ይችላሉ፣ ሆቴልን መያዝም ይችላሉ ተብሏል።
አሁን ላይ በቱሪዝም ዘርፍ ተወዳዳሪ ለመሆን ከተፈለገ አሰራርና መረጃዎች ዲጂታል ማድረግ ያስፈልጋል ቴክኖሎጂውም የተጠቃሚው ደህንነት የጠበቀ ሊሆን ይገባል፣ መተግበሪያውም ይህንን መስፈርት ያሟላ ነው ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ የመረጃ መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ትዕግስት ሃሚድ ናቸው።
በድረ ገፁ ላይ የተለያዩ ሆቴሎች፣ አስጎብኚ ማህበራት እና ሌሎችም አገልግሎት ሰጪዎች እራሳቸውን ማስተዋወቅና መረጃቸው ማስገባት ይችላሉ ተብሏል።
አሁን ባለ ኮከብ ሆቴሎች በድረ ገፁ መካተታቸውንም ተነግሯል።
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments