top of page

ሐምሌ 2፣ 2016 - በአበዳሪ ድርጅቶች አና ሀገራት መከካል ያለው ግኑኝነት ምንድነው?

  • Jul 9, 2024
  • 1 min read

ኢትዮጵያ ከአበዳሪ ተቋማት 10.5 ቢሊዮን ዶላር ብድር ለማግኘት መቃረቧን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መናገራቸው ይታወሳል፡፡


ስም ሳይጠቅሱ አንዳንድ ወዳጅ ሀገሮች ባደረጉት ድጋፍ አብዛኛው ሀሳቦቻችን ተቀባይነት እያገኙ ይመስላል ሲሉ የተናገሩት ጠ/ሚኒስትሩ ይህ የሚሳካ ከሆነ ኢትዮጵያ ተጨማሪ 10.5 ቢሊዮን ዶላር በሚቀጥሉት ዓመታት ታገኛለች ብለዋል፡፡


ኢትዮጵያ አጠቃላይ እዳዋ የሀገር ውስጡም የውጭውም ተደማምሮ 65.7 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ከዚህ ውስጥ 34 በመቶው ወይንም 22.36 ቢሊዮን ዶላሩን የተበደሩት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ናቸው፡፡


ሀገሪቱ በአጭር ጊዜ ከሚመለሱ እና ወለዳቸውም ከፍተኛ ከሆኑ (Commercial loan) የመመለሻ ጊዜያቸው ረጅም እና የወለድ መጠናቸው ዝቅተኛ ወደሆኑ የብድር ዓይነቶች(Concessional loans) ፊቷን አዙራለች መባሉም ይታወሳል፡፡


በስልጣን ላይ ያለው አስተዳደር አንዲትም የመመለሻ ጊዜው አጭር እና ወለዱ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ አልተበደርኩም ሲል በተደጋጋሚ ይሰማል፡፡


ከሚነገሩት የብድር ዓይነቶች ለኢትዮጵያ አብዝቶ የሚጠቅመው የትኛው ነው?



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page