ሐምሌ 18 2017 - የኢትዮጵያ ልጆች ኢትዮጵያዊ ለዛ ባለው መልኩ የሚዝናኑበት፣ የሚማሩበት፣ የሚጫወቱበት መተግበሪያ ተሰርቶላቸዋል ተባለ።
- sheger1021fm
- Jul 25
- 1 min read
መተግበሪያው“የኢትዮጵያ ልጆች ሱፐርአፕ (Ethiopia Lijoch Supper App) የሚባል ሲሆን ከቅድመ መደበኛ እስከ አራተኛ ክፍል ላሉ ልጆች የተማሩትን በጨዋታ መልክ የሚከልሱበት፣ የሚያጠኑበትን ይዘት እንዳለው ተነግሯል።
ተማሪ ቤት፤ ቤተ መጻሕፍት፣ ሥነ-ምግባር፣ ጠፋጭ ታሪኮችን ጨምሮ ከ10 ዓይነት በላይ ይዘቶችን የኢትዮጵያ ልጆች ሱፐር አፕ ማካተቱን ሰምተናል።
ወለጆች መተግበሪያውን ( ethiolijoch.com/app ) ላይ ገብተው በማውረድ በስልካቸው ላይ በመጫን ልጆቻቸውን ማስጠቀም ይችላሉ ተብሏል።

መተግበሪያው ለጊዜው የሚሰራው በአንድሮይድ ስልኮች ላይ መሆኑን መተግበሪያውን የሰራው መሀቡብ ቴክኖሎጂስ ነግሮናል።
ይህንን መተግበሪያ ለመጠቀም ለስድስት ወር 600 ብር ለአንድ ዓመት ደግሞ 1,000 ብር መክፈል እንደሚያስፈልግ ተነግሯል።
ወላጆች ይህንን አፕሊኬሽን ለልጆቻቸው የሚያስጠቅሙ ከሆነ ልጄ ያልተገባ ነገር ያይብኛል ብለው ሳይሳቀቁ ልጆቻቸውን እየተዝናኑ እንዲያውቁ ያስችላቸዋል ተብሏል።
ወላጆች የልጆቻቸው የስክሪን ቆይታም በፈለጉት ቦታ ሆነው መቆጣጠርና መገደብ የሚያስችላቸው ስርዓትም መተግበሪያው መያዙንም ሰምተናል።
መተግበሪየውን የሰራው መሀቡብ ቴክኖሎጂስ ሲሆን በመተግበሪያው ላይ ያሉት ይዘቶች የሚሰራው ደግሞ የኢትዮጵያ ልጆች ሚዲያ ነው።
መተግበሪያውም በትናንትናው ዓለት ተመርቋል።
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
Comments