top of page

ሐምሌ 17 2017 - ኢትዮ ቴሌኮም ዘንድሮ 162 ቢሊየን ብር ገቢ አግኝቻለሁ አለ።

  • sheger1021fm
  • Jul 24
  • 1 min read

በቴሌኮም ዘርፍ ደንበኛን ማቆየት በጣም ፈታኝ ነው ያሉት የኩባንያው ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በተለያዩ አገልግሎቶች ደንበኞቻችንን አቆይተናል ብለዋል።


በዚህም አጠቃላይ የደንበኞች ቁጥር 83.2 ሚሊየን ደርሷል ተብሏል፤ ይህም ከአምናው በ6.2 በመቶ ጨምሯል።


በኢትዮዽያ የመጀመርያው የ’ሞባይል መኒ’ አገልግሎት የሚሰጠው #ቴሌብር በ4 ዓመት ጉዞው ውስጥ በከፍተኛ ቁጥር ከደንበኞች እና ከሀገር ጋር ተላምዷል ተብሏል።


የቴሌ ብር ደንበኞች ቁጥር 54.8 መድረሱን ሰምተናል።


አገልግሎቱ ከተጀመረ ጊዜም አንስቶ 4.9 ትሪሊየን ብር ተገላብጧል ተብሏል።


በዚህ ዓመትም ቴሌ ብር 7 ሚሊየን ደንበኞችን በማፍራት 2.8 ትሪሊየን ብር ተላውሶበታል ተብሏል።


ቴሌ ብር አገልግሎት ከጀመረ አንስቶ 11.9 ሚሊየን ደንበኞች 25.8 ቢሊየን ብር መበደራቸውን ሰምተናል።


ይህ ቁጥር የዲጂታል ኢኮኖሚን ግንባታ የሚያስረዳ ነው ሲሉ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል።


ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Recent Posts

See All
ጥቅምት 20 2018 - የፍትህ ስርዓት ችግር ምክንያት ስራው ላይ እክል እየገጠመው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ

የሚሰጣቸውን ምክረ ሃሳቦች ያለ በቂ ምክንያት የማይፈፅሙ ተቋማት በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ቢሞክርም ባለው የፍትህ ስርዓት ችግር ምክንያት ስራው ላይ እክል እየገጠመው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ፡፡ ተቋሙ የአስተዳደር በደል ደረሰብን እምባችን ይታበስልን የሚሉ አቤት ባዮችን ቅሬታ በመቀበል

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page