top of page

ሐምሌ 17 2017 - በሴቶች ላይ የሚሰሩ የተለያዩ ማህበራት ''ሀገራዊ ምክክር እንዲደረግባቸው የለየናቸው ጉዳዮች ትኩረትም እንዲደረግባቸው'' ሲሉ ጠየቁ

  • Jul 24, 2025
  • 1 min read

በሴቶች ላይ የሚሰሩ የተለያዩ ማህበራት ሀገራዊ ምክክር እንዲደረግባቸው የለየናቸው ጉዳዮች እንዳይወጡ፣ ትኩረትም እንዲደረግባቸው ሲሉ ጠየቁ፡፡


የሀገራዊ ምክክሩ በበኩሉ የሴቶች ጉዳይ ትኩረት የማያገኝበት ምንም ምክንያት የለም ሲል አስረድቷል፡፡


የሴቶች ማህበራቱ ዋና ዋና እና አንገብጋቢ ናቸው ብለው ለኮሚሽኑ ካስገባቸው አጀንዳዎች መካከል የሰላምና የፖለቲካ አለመረጋጋት የሚሉት ይገኙበታል፡፡

የሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትና የመሬት ባለቤትነት መብት ውስንነት፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች፣ የኑሮ ውድነትና የስራ አጥነት ችግር በሴቶች ላይ የሚፈጥረው ጫና ከብዙ በጥቂቶቹ ናቸው፡፡


የገቡት አጀንዳዎች አጀንዳ ብቻ ሆነው እንዳይቀሩ የሁሉም አካላትን ድጋፍ የሚጠይቅ ነው ሲሉ የሴቶቹ ተወካይ የሆኑት ወ/ሮ አሚን መሃመድ ተናግረዋል፡፡


የሴቶችን አጀንዳ ከተለያዩ ክልሎች ማሰባሰቡ ጠቀሜታው የጎላ ቢሆንም ሴትን የተመለከቱ አጀንዳዎች ትኩረት ሲሰጣቸው አይታይም ያሉት ደግሞ የጥምረት ለሴቶች በሃገራዊ ምክክር መድረክ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሳባ ገ/መድህን ናቸው፡፡


የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በበኩሉ ኮሚሽኑ ትኩረት ያስፈልጋቸዋል ካላቸው መካከል ሴቶች፣ አካል፣ ጉዳተኞችና ወጣቶች መሆናቸውን ተናግሯል።


በአጀንዳ ማሰባሰብ ወቅት የሴቶች አጀንዳ በአግባቡ እንዲካተት ሲሰራ የነበረው ኮሚሽኑ የአጀንዳ ቀረፃ ሲካሄድ ትኩረት እንዳያገኙ የሚያደርግበት ምክንያት የለውም ሲሉ ነገሩን የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጥበቡ ታደሰ ናቸው፡፡



ማርታ በቀለ

Recent Posts

See All
የኤሌክትሪክ ታሪፍ በየጊዜው ሲጨምር ይታያል፡፡

ነሐሴ 7 2018 የኤሌክትሪክ ታሪፍ በየጊዜው ሲጨምር ይታያል፡፡ በዚህም ደንበኞች ቅሬታ ያቀርባሉ ፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበኩሉ አዲስ የታሪፍ ጭማሪ አለማድረጉን፤ የአሁኑ የዋጋ ለውጥ ከ2017 ጀምሮ በ16 ዙር ለማስፈጸም የታቀደው አሰራር አካል ነው ብሏል፡፡ እንደውም ከሁለት አመት በፊት ተግባራዊ ያ

 
 
 
ዛሬ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ባደረገው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ በ161 ብር ከ79 ሳንቲም መሸጡ ተነገረ፡፡

ነሐሴ 6 2018 ዛሬ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ባደረገው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ በ161 ብር ከ79 ሳንቲም መሸጡ ተነገረ፡፡ ዛሬ ይፋ በሆነው ጨረታ 125 ሚሊዮን ዶላር ለጨረታ ቀርቧል ተብሏል፡፡ በጨረታው 28 ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን በጨረታው የድርሻቸውን ተጫርተው የወሰዱ ባንኮች ቁጥር 9 መሆ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page