top of page

ሐምሌ 10 2017 - ምሁራን በጥናትና ምርምር ደረስንበት ብለው የሚያወጡት የጥናት ውጤት ምን ያህል የፖሊሲ ግብዓት ይሆናል?

  • sheger1021fm
  • Jul 17
  • 1 min read

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ በየጊዜው ምርምር የሚያደርገው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሲዬሽን በምርምር ስራዎቹ ዙሪያ የሚመክርበት 22ኛ ጉባኤውን ለማድረግ እየተሰናዳ ነው።


የኢትዮጵያ የኢኮኖሚክስ አሶሼሽን በዘንድሮው ዓለም አቀፍ ጉባኤው በዝቅተኛ የደመወዝ ወለል፣ በኢትዮጵያ የታክስ ሥርዓትና በሌሎች ከ10 በላይ የሚሆኑ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ዙሪያ ጥናትና ምርምር እንደሚያቀርብ ሰምተናል።


ጉምቱ የማክሮ ኢኮኖሚ ተመራማሪዎች የሚሰጡት የምርምር እና የጥናት ወረቀቶችን ፤ መንግስት ተቀብሎ ለፖሊሲ ግብአት ይጠቀምበታል ወይ ተብሎ ይጠየቃል።


ውሳኔ አሳላፊዎች ፖሊሲ ቀራጮች ከዚህ ቤት የወጣውን እና በብርቱ የተደከመበትን የምርምር ውጤት ቢጠቀሙት ይበጃል ተብሎም ሲመከር ይሰማል።


ለመሆኑ እስካሁን የተሰሩ ምርምሮችና ውጤቶቹ ምን ያህል የፖሊሲ ግብዓት ሆነዋል፤ የምታቀርቡት ምክረ ሀሳብስ ከሀሳብ አልፎ ተግባራዊ እየተደረገ ነው ወይ? ብለን ጠይቀናል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ……..


ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page