top of page

ህዳር 19፣2017 - ''ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች አምቡላንሶች እየወደሙ በጤናው ዘርፍ መስተጓጉሎች እየተፈጠሩ ነው'' የጤና ሚኒስቴር

  • sheger1021fm
  • Nov 28, 2024
  • 1 min read

ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች አምቡላንሶች እየወደሙ በመሆኑ በጤናው ዘርፍ መስተጓጉሎች እየተፈጠሩ ነው ሲል የጤና ሚኒስቴር ተናገረ፡፡


በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ የአምቡላንስ እጥረት እንዳለ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተናግረዋል፡፡


በዚህም የተነሳ እናቶች በወሊድ ወቅት እየተቸገሩ እንዲሁም ሌሎች ታማሚዎችም ከአንድ የጤና ተቋም ወደ ሌላው ለማዘዋወር ከፍተኛ ችግር እያጋጠመ ነው ተብሏል፡፡


እንደራሴዎች ይህንን ችግር ለመፍታት የጤና ሚኒስቴር ምን እየሰራ እንደሆነ ጠይቀዋል፡፡

ree

የጤና ሚኒስትር መቅደስ ዳባ(ዶ/ር) በሀገሪቱ የአምቡላንስ እጥረት ከመኖሩም ባሻገር በተለይም ግጭት ባለባቸው ቦታዎች የሚገኙ አምቡላንሶች መውደማቸው ተጨማሪ ችግር እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡


እንደ ሀገር የገጠመውን የአምቡላንስ እጥረት ችግር ለመቀነስ መስሪያ ቤታቸው የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሆ አስረድተዋል፡፡

ree

ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ጤና ሚኒስቴር  3,014 አምቡላንሶችን ገዝቶ በሁሉም ክልል ለሚገኙ የጤና ተቋማት አከፋፍሏል ብለዋል፡፡


በተጨማሪ እንደ አምቡላንስ ሆነው ድጋፍ የሚሰጡ ከ200 በላይ ፒክአፕ መሰል ተሽከርካሪዎችም ተሰራጭተዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡


የጤና ተቋማት ራቅ ለሚልባቸው ነዋሪዎች የሚሆኑም 572 ሞተር ሳይክሎች ተከፋፍለው የጤናው ዘርፍ አገልግሎት እንዲያግዙ ተደርጓል ብለዋል ሚኒስትሯ፡፡


ማንያዘዋል ጌታሁን

Recent Posts

See All
ወደ ቀድሞ ቀያቸው ሄደው እንደገና ወደ ደብረብርሃን የተመለሱ ተፈናቃዮች መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡ 

ታህሳስ 11/2018   ወደ ቀድሞ ቀያቸው ሄደው እንደገና ወደ ደብረብርሃን የተመለሱ ተፈናቃዮች መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡   የአማራ ክልል የአደጋ ስጋት መስሪያ ቤት በጉዳዩ ላይ መልስ ለመስጠት አልፈቀደም።   ከመንግስት የሚቀርበውን ድጋፍ ለተፈናቃዮች የሚያከፋፍለውና ሌሎች ስራዎችን የሚሰራው በመንግስት የተቋቋመ ኮሚ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page