ጥቅምት 5፣2017 - በአዲስ አበባ የሚሰሩ ሚኒ-ባሶች፣ ሚዲ-ባስ ታክሲዎች እና የከተማ አውቶብሶች የታሪፍ ጭማሪ እንደሚያደርጉ ተነገረ፡፡
- sheger1021fm
- Oct 15, 2024
- 1 min read
በአዲስ አበባ የሚሰሩ ሚኒ-ባሶች፣ ሚዲ-ባስ ታክሲዎች እና የከተማ አውቶብሶች የታሪፍ ጭማሪ እንደሚያደርጉ ተነገረ፡፡
በአዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ጭማሪ እንደሚደረግ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ተናግሯል፡፡

የታሪፍ ጭማሪው ከነገ ጥቅምት 5፣2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ነው የተሰማው፡፡
የታሪፍ ጭማሪው፤ የአዲስ አበባ ከተማ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ለተሰማሩ ሚኒ-ባሶች፣ ሚዲ-ባስ ታክሲዎችና የከተማ አውቶብሶችን ያጠቃልላል ተብሏል፡፡
የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ ወቅታዊ የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ እና ሌሎች አስተዳደራዊ ወጪዎችን ያማከለ ነው ብሏል ቢሮው፡፡
የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች አዲስ የተሻሻለው ህጋዊ የታሪፍ ተመንን በሚተላለፉት አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድም አሳስቧል፡፡
ቀድሞ አገልግሎት ሲሰጥበት የነበረው የታሪፍ ተመን ከጥቅምት 20/2016 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት ላይ የዋለ ነበረ፡፡
Kommentare