top of page

ግንቦት 30፣2016 - ከራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ እና ሌሎች የአካባቢው ወረዳዎች የተፈናቀሉ ከ 67,000 በላይ ሰዎች መጀመሪያ ቆቦ ላይ አሁን ደግሞ ዋጃ ላይ ሰፍረው ይገኛሉ

  • sheger1021fm
  • Jun 7, 2024
  • 1 min read

የአማራ እና የትግራይ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ የሚያነሱባቸው አካባቢዎች ከጦርነቱ በኋላ የተቋቋሙ አስተዳደሮች እንዲፈርሱ እና የፌደራል የፀጥታ ተቋማት ለአካባቢዎቹ ዘላቂ መፍትሄ እስኪሰጥ ፀጥታ እንዲያስከብሩ ስምምነት ተደርሷል መባሉ ይታወሳል፡፡


በዚሁ መሰረት የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ እና ሌሎች የአካባቢው ወረዳዎች የመንግስት አገልግሎት ቆሟል፡፡


በዚህም ስድስት የወረዳ አስተዳደሮች የመንግስት ሆነ የግል አገልግሎት ተቋማት ስራ ካቆሙ ሁለት ወር ሆኖቸዋል መባሉን ሰምተናል፡፡


ከሶስት ወረዳዎች የተፈናቀሉ ሰዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን የአላማጣ ወረዳ አስተዳዳሪ ለሸገር ተናግረዋል፡፡


ከዚህ ቀደም በነበረው የሰሜኑ ጦርነት መማር አለብን ያሉት አስተዳዳሪው ህዝቡ መጎዳት የለበትምም ብለዋል፡፡

ተፈናቃዮቹ እኛ ቤት ንብረት ያለን አርሰን የምናድር በመሆናችን የምንፈልገው በመጠለያ ሆኖ መረዳትን ሳይሆን ወደ ቀያችን ተመልሰን የፀጥታው ሁኔታ ተረጋግጦልን መኖር ነው ሲሉ ነግረውናል፡፡


በወሰን ይገባኛል የተነሳ የተለያየ ችግር የሚደጋገምበት የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ እና ሌሎች የአካባቢው ወረዳዎች የተፈናቀሉ ከ 67,000 በላይ ሰዎች መጀመሪያ ቆቦ ላይ አሁን ደግሞ ዋጃ ላይ ሰፍረው ይገኛሉ፡፡


ማርታ በቀለ



Comentarios


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page