ደንበኞች ባሉበት ሆነው የእጅ ስልካቸውን በመጠቀም ብቻ የቆጣሪ ንባባቸውን የሚያስገቡበት አሰራር በሙከራ ደረጃ መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አግልግሎት ተናገረ፡፡
- Mar 6
- 1 min read
የካቲት 27/2018
ደንበኞች ባሉበት ሆነው የእጅ ስልካቸውን በመጠቀም ብቻ የቆጣሪ ንባባቸውን የሚያስገቡበት አሰራር በሙከራ ደረጃ መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አግልግሎት ተናገረ፡፡
ይህም በተደጋጋሚ ከደንበኞች የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት ይረዳኛል ብሏል።
የሙከራ ትግበራው ከ16 ሺህ በላይ የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች ባሉበት የሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን መጀመሩን የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ አንዋር አብራር ነግረውናል ፡፡

ሥራ አስፈፃሚው የዲጂታል አሰራሩ ለደንበኞች በቀላሉ ተደራሽ ለመሆን፣ የፍጆታ ሂሳብን በወቅቱ ለመፈጸም፣ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም ጊዜና ወጪን ለመቆጠብ ያስችላል ብለውናል፡፡
በዚህም ከየካቲት 13 ቀን እስከ የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ደንበኞች የፍጆታ ንባባቸውን በቀላሉ በቤታቸው ሆነው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ የቴሌግራም ቻትቦት ላይ ሲልኩ እንደነበር ከኃላፊው ሰምተናል።
በሙከራ ደረጃ የተጀመረው አሰራር ያሉበትን ክፍተቶች እና ጥንካሬዎች በመለየት በቀጣይ በሌሎች ሪጅኖች እና የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለማስፋት መታቀዱንም አቶ አንዋር አብራር ነግረውናል፡፡
ንጋት መኮንን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





I found the article on the "password game" quite insightful, especially how it's streamlining the customer service process. It's fascinating to see how Ethiopia's electrical utility is adapting to modern challenges.
I appreciate the insights shared in this blog about the evolving landscape of technology and service, especially in Ethiopia. It resonates with my own experience navigating digital shifts. I often find myself playing FNAF as a way to unwind, reflecting on how quickly our attention spans have changed alongside tech advancements. While we adapt to these new systems, it’s crucial we foster connections that keep us grounded, just like those moments when I finally beat my high score!