top of page

የአዕምሮ ህክምና አገልግሎቱ ካለፉት ዓመታት እየተሻሻለ ቢመጣም አሁንም ግን እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎችን ያህል በስፋት አልተሰራበትም ተባለ

የአዕምሮ ህክምና አገልግሎቱ ካለፉት ዓመታት እየተሻሻለ ቢመጣም አሁንም ግን እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎችን ያህል በስፋት አልተሰራበትም ተባለ፡፡


መሰረታዊ የሆኑ የስነ-ልቦና የምክር አገልግሎትን ጨምሮ የመጀመሪያ ደረጃ የአዕምሮ ህክምና አገልግሎቶች በየጤና ተቋማት መሰጠት መጀመሩ የታየ ለውጥ ነው ተብሏል፡፡


ካለፉት ዓመታት አኳያ የአዕምሮ ጤና ህክምናው ላይም ይሁን የባለሞያዎቹ ቁጥር ከፍተኛ መሻሻል መኖሩን የነገሩን የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስቱ አታላይ አለም(ፕ/ር) ናቸው፡፡


ነገር ግን በሀገሪቱ ካለው የአዕምሮ ህክምና አገልግሎት ፈላጊ ጋር ሲተያይ አሁንም ቁጥሮቹ ትንሽ ናቸው ብለዋል፡፡


በተለይ ከመድኃኒት አቅርቦት ጋር እንዲሁም ቅድሚያ እንደተላላፊ ላሉ ህመሞች ከመሰጠቱ አኳያ የአዕምሮ ህክምናው የተገባውን ያህል ትኩረት አልተሰጠውም ተብሏል፡፡


በኢትዮጵያ ከአራት ሰዎች አንዱ ቢያንስ በህይወቱ አንድ ጊዜ የአዕምሮ ህመም እንደሚያጋጥመው የተነገረ ሲሆን ይህም ከአጠቃላይ ህዝብ 24 በመቶ እንደሆነ በሀገሪቱ በአዕምሮ ጤና ላይ የተሰራ ጥናት ያሳያል፡፡

ምህረት ስዩም


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page