top of page

ነሀሴ 1፣2016 - በማሻሽያው ምክንያት እውነት መንግስት እንዳለው፤ ሀገሪቱ ወደ ውጭ የምትልካቸው ምርቶች እና የውጭ ምንዛሪ ግኝቱ ይጨምር ይሆን?

ኢትዮጵያ በቅርቡ ይፋ ያደረገችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሽያ አንዱ ያሳካል የተባለው አንዱ የውጪ ንግድን ነው፡፡


ይህ ማሻሽያ ሀገሪቱ አምርታ፤ ባህር አሻግራ የውጭ ምንዛሬ የምታገኝባቸውን ምርቶች በመጠንም በዓይነትም እንደሚጨምር ያስረዳል፡፡


እውነት ሰነዱ እንዳለው መንግስትም እንዳስረዳው፤ በማሻሽያው ምክንያት ሀገሪቱ ወደ ውጭ የምትልካቸው ምርቶች እና የውጭ ምንዛሪ ግኝቱ ይጨምር ይሆን?


በኢትዮጵያ ወጪ እና ገቢ ንግድ መካከል ያለው ልዩነት ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሆነ ይነገራል፡፡


ሀገሪቱ አምርታም ይሁም አርሳ አብቅላ ወደ ውጪ ልካ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ያገኝችው ከሁለት ዓመት በፊት ሲሆን እሱም ከ4 ቢሊዮን ዶላር ነበር ይህም በታሪክ የመጀመሪው እና ከፍተኛው እንደሆነ በወቅቱ ተነግሮ ነበር፡፡


ከዚያ ወዲህ ባሉት ሁለት ዓመታት ግን የወጪ ንግድ ገቢው 3.8 እና 3.6 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡


ነዳጅ፣ የአፈር ማደበርያ እና የተለያዩ ምርቶችም ከውጭ ለማስገባት ደግሞ በየ ዓመቱ በአማካኝ 13 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደምታወጣ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡


በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሞያዎች ማህበር የፖሊሲ ትንተና እና የጥናት ዳይሬክተር ዶ/ር ድግዬ ጎሹ፤ ማሻሽያው በታሰበው ፍጥነት የወጭ ንግድን ማሳደግ እንደማይችል ያስረዳሉ፡፡


«አሁን ትልቁ ነገር በአጭር ጊዜ ውስጥ export (የወጪ ንግድ) አይጨምርም ዋነኛው ምክንያት የሀገር ውስጥ የማምረጥ አቅማችን ‘’stagnated’’ ነው፤ መነቆ ውስጥ ነው ብለዋል፡፡


«ምክንያቱ ደግሞ በሀገሪቱ ውስጥ ባለው ግጭት እና ከፖለቲካ አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ ትራንስፖርት፣ መሰረተ ልማት፣ የሰው ሃይል፣ በሙሉ አቅም እየተጠቀምን አይደለም፤ አይሲቲም ለስንት ወራት በአስቸኳይ አዋጅ ምክኒያት እና ሌሎቸም አብዛኞቹ የማምረት አቅሞቻችን ‘’stagnated’’ ስለሆኑ እነሱን አላቀን ፈተን መነቆቸውን አንስተን ወደ ሙሉ የማምረት አቅማችን ገብተን በዙ ማምረት ካቻልን የወጪ ንግድ ሊጨምር አይችልም ይላሉ፡፡»


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comments


bottom of page