ከተሞች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፉ፣ የነዋሪዎችም ቁጥር እያሻቀበ ቢሄድም ለመኖረያ ቤት ግንባታ፣ ለእርሻ፣ለመሰረተ ልማት፣ ለኢንቨስትመንት እና ለሌሎችም አገልግሎቶች የሚውለው የሀገሪቷ የመሬት ሀብት አጠቃቀም ስርአት ግን ጊዜውን የሚመጥን እንዳልሆነ ይነገራል፡፡
ለዚህም ከጊዜው ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፍላጎት ጋር የሚሄድ ምቹ የህግ ማዕቀፍ በመፍጠርና የመሬት ጥበቃ እና አጠቃቀምን በማዘመን፣ ከመሬት ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመቀነስ ሁሉም በፍትሃዊነት ተጠቃሚ የሚሆንበት ዘመናዊ #የመሬት_አስተዳደር_ፖሊሲ በሀገሪቱ መዘርጋት እንዳለበት ባለሞያዎች ይመክራሉ፡፡
በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና የህግ ተመራማሪ ዳንኤል በኃይሉ(ዶ/ር) የኢትዮጵያን የመሬት ፖሊሲ በተመለከተ ጥናት እና ምርምር አድርገዋል፡፡
ባለሙያው ‘’የመሬት ስሪት እንጂ ኢትዮጵያ የስነ-ምህዳር ቀጠናዎችን ያገናዘበ የመሬት ይዞታን ጠብቆና አልምቶ ለትውልድ ማስተላለፍ የሚያስችል ዘላቂ ፖሊሲ የላትም’’ ይላሉ፡፡

ሀገሪቷ የተፈጥሮ ሀብትና መሬትን ተጠቅማ እንዴትና ምን ማከናወን እንዳለባት በዝርዝርና በጥልቀት የሚተነትን የመሬት ፖሊሲ ማጣቷ እስከዛሬም ድረስ ላልተላቀቃት ድህነት እና ጦርነት አንዱ መነሻ እንደሆነ የጥናት እና ምርምር ባለሙያው ዳንኤል በኃይሉ(ዶ/ር ) ያስረዳሉ፡፡
ባለሙያው አድርጌዋለሁ በሚሉትና በዘርፉ ምሁራኖች ተገምግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባለድርሻነት በታተመው የመሬት ፖሊሲ ጥናት እና ምርምራቸው ላይ ኢትዮጵያ ባለብዙ ይዞታ(multi tenure) የፖሊሲ ስርአትን ብትጠቀም የሚል ምክረ ሃሳብ ማቅረባቸውንም ነግረውናል፡፡
የባለብዙ ይዞታ(multi tenure) የመሬት ፖሊሲ ስርአትን ከሚጠቀሙ የአፍሪካ ሀገራት ሩዋንዳን በአብነት ያነሱት ባለሞያው ከኢትዮጵያ 35 በመቶ ያነሰ ይዞታ ያላት ሩዋንዳ በመሬት ሃብት ልውውጥ ብቻ በዓመት 12 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘት እንደቻለች አመሳክረዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/273vu79u
ንጋት መኮንን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments