ሌብነትን ወይም ሙስናን ለማስቀረት በሚል የሀብት ማስመዝገብ ስራ ከ14 ዓመታት በፊት መጀመሩ ይታወሳል፡፡
የሀብት ምዝገባውም ከወረቀት አሰራር ወደ ኢንተርኔት መላ ተሸጋግሯል ተብሎም ነበር፡፡
በህንዳዊያን የተሰራ የኦንላይን #ሀብት_ማስመዝገብ መላ ግን ጥቂት ዓመታት ሰርቶ ተቋርጦ ቆይቷል፡፡
አሁን በስራ ላይ የዋለው መተግበሪያ በኢትዮጵያውያን የተሰራ ነው ተብሏል፡፡
ቴክኖሎጂው ሀብትን ከመዘገበ በኋላ ማረጋጋጫ ሰርተፍኬት እንደሚሰጥ ከፌዴራል #የፀረ_ሙስና ኮሚሽን ሰምተናል፡፡
ሀብት ማስመዝገብን የመንግስት ተሿሚዎች፣ ተመራጮች ብቻ ሳይሆን የግል ተቋማት እና ሰዎችም ያስመዘግባሉ ተብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comentários