ኢትዮጵያ ቢዝነስን አቀላጥፎ ለመስራት (Ease of Doing Business) የማትመች፣ ጥልፍልፍ አሰራሮች ያሉባት መሆኑ ያለችባት ደረጃ ያሳያል፡፡
የአለም ባንክ ሪፖርት እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ #ቢዝነስን አቀላጥፎ ለማከናወን በሚያስችሉ አለም አቀፍ መመዘኛዎች ከ190 ሀገራት ደረጃዎች 159ኛ ላይ ነው፡፡
በጥንታዊነቷ፣ ንግድንም ቀድሞ በመጀመር፣ መገበያያንም በማኖር ቀድሞ ስሟ የሚጠቀሰው ኢትዮጵያ ስራ (ቢዝነስ) ለመስራት ያላት አመቺነት ግን ዝቅተኛ ወይም ከአለም ሀገር ከ31 ብቻ የተሻለ ነው፡፡
ለአብነትም በኢትዮጵያ #የንግድ_ምዝገባ ለማከናወን 32 ቀናትና 11 መስፈርቶችን ማሟላት ይጠይቃል ይላል የአለም ባንክ ሪፖርት፡፡
በኢትዮጵያ በግልም ይሁን ከሌሎች ጋር ሆኖ ሀሳብን አዋጥቶ ገንዘብ መስሪያ ቦታ ፈልጎ ስራ ሰርቶ ትርፋማ ለመሆኑ አድካሚ መንገዶችን መጓዝ ይጠይቃል፡፡
የበዛ የህዝብ ቁጥር፣ ስራ አጥ በበዛበት ሀገር፣ ስራ መስሪያው መንገድ ግን ለምን በመርፌ ቀዳዳ የማለፍን ጥበብ የሚጠይቅ ሆነ?
ከ4 እና አምስት ዓመታት በፊት ቢዝነስን አቀላጥፎ ለመስራት እንቅፋት የሆኑ አሰራሮችን ለመፍታት ይሰራል ተብሎ ፣ ጉዳዩም በከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ጭምር የሚነገር ነበር፡፡
ቢያንስ ሀሳብ ያለው ገንዘብ ያለማስያዝ እንዲያገኝ፣ ስራ ለመጀመር #የቤት_ኪራይ ውል ስምምነት ግዴታ እንዳይሆን መንገዱን ማቅለል ታስቦም፣ ይሰራልም ተብሎ ነበር፡፡
ዛሬም ግን ብዙ የተለወጠ ነገር አይታይም፡፡
አቶ ከፈለኝ ሀይሉ ዛሬም በኢትዮጵያ የቢዝነስ ሀሁ ያስፈልጋል ብለው ያምናሉ፡፡ ለዚህም "የቢዝነስ ሀሁ በኢትዮጵያ" የሚል መፅሐፍ ፅፈዋል፡፡ በሞያቸውም የቢዝነስ አማካሪ ናቸው፡፡
አቶ ከፈለኝ ቢዝነስ ከማገዝ ይልቅ ቁጥጥርን ያስቀደሙ አሰራሮች መንገዱን እንዳከበዱት ያስረዳሉ፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
ንጋቱ ሙሉ
Comments