top of page

ሰኔ 7፣ 2016 - በአዲስ አበባ ከሚገኙና የባህል ህክምና ከሚሰጡ ተቋማት ውስጥ በህጋዊ ተመዝግበው አገልግሎት የሚሰጡት 86ቱ ብቻ ናቸው ተባለ

በአዲስ አበባ ከሚገኙና የባህል ህክምና ከሚሰጡ ተቋማት ውስጥ በህጋዊ ተመዝግበው አገልግሎት የሚሰጡት 86ቱ ብቻ ናቸው ተባለ፡፡


ከዚህ ውጪ ያሉና በከተማዋ የባህል ህክምና እንሰጣለን የሚሉትን አላውቃቸውም ሲል የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ተናግሯል፡፡


የባህል ህክምና ዘርፉ በአግባቡ ቢሰራበት ከዘመናዊው የህክምና ሥርዓት ጋር ተጣምሮ ለብዙዎች ጠቃሚ እንደሚሆንም ተነግሯል፡፡


የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ከከተማዋ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ጋር በመሆን በአዲስ አበባ የባህል ህክምና አገልግሎቱ ጥቅም ላይ እንዲውል ከባህል ህክምና አዋቂዎች ማህበራት በተገኙበት አውደ ጥናት አካሂዷል፡፡


አግባባዊ የባህል መድኃኒት አጠቃቀሙን በተመለከተ በዘርፉ ህጋዊ ሆነው የሚሰሩ ቢኖሩም በባህል ህክምና ስም ያልተገቡ እና የሰዎችን ጤና ለጉዳት የሚዳርጉ የተለያዩ ህገወጦች መበራከታቸውን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊው ዶ/ር ዮሐንስ ጫላ ተናግረዋል፡፡


ለዚህም በከተማዋ በባህል ህክምና ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች በህጋዊነት እና ኃላፊነት ወስደው እንዲሰሩ ማድረግ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡


በአዲስ አበባ በህጋዊነት በተቆጣጣሪው አካል ተመዝግበው እየሰሩ ያሉ 86 የባህል ህክምና አዋቂዎች ማህበራት መኖራቸውንና በህጋዊ ስም ያልተገባ የሚፈጽሙ በርካታ ግለሰቦች መኖራቸውን የተናገሩት ደግሞ የአዲስ አበባ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ስራ አስኪያጇ ሙሉእመቤት ታደሰ ናቸው፡፡



Commentaires


bottom of page