ሰኔ 16 2017 -የኢትዮዽያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ደንበኞች የኢንቨስትመንት ሂሳብ አካውንት እንዲከፍቱ ጥሪ አቀረበ
- sheger1021fm
- 5 days ago
- 1 min read
የኢትዮዽያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች፤ገበያው ተከፍቶ ግብይት እየተከናወነ በመሆኑ ደንበኞች የኢንቨስትመንት ሂሳብ እንዲከፍቱ ጋብዟል።
የኢትዮዽያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጥላሁን እስማኤል(ዶ/ር) ገበያው በተፈለገው እቅድ እና መንገድ እየሄደ መሆኑን ተናግረው ባንኮች እና ሌሎች ድርጅቶችም በዚሁ ገበያ እየተመዘገቡ መሆኑን አስረድተዋል።
ደንበኞች የኢንቨስትመንት ሂሳብ አካውንት እንዲከፍቱ የጋበዙት ዋና ስራ አስፈፃሚው ናቸው።
ይህ የተሰማው ዛሬ የገዳ ባንክ በኢትዮዽያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ላይ ሶስተኛው ድርጅት በመሆን በተመዘገበበት ጊዜ ነው።
ባንኩ የደንበኛ ሳቢ መግለጫውን በኢትዮዽያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ካስመዘበገ በኋላ በሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ ቀርᎆል ተብሏል።

የገዳ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ቡልቶ ባንኩ በዚህ ገበያ በመመዝገቡ ባለአክስዮኖች ሰፊ የገንዘብ እንዲኖራቸው እና የ ፋይናንስ ተደራሽነት እንዲሰፋ ያደርጋሉ ብለዋል።
በኢትዮዽያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ኢትዮ ቴሌኮም፤ ወጋገን ባንክ እና ገዳ ባንክ የተመዘገቡ ድርጅቶች ናቸው።
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Commentaires