ሚያዝያ 21፣2016 - የ12ተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ
- sheger1021fm
- Apr 29, 2024
- 1 min read
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2016 የትምህርት ዘመን የ12ተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀንን ይፋ አድርጓል፡፡
ፈተናው ለማህበራዊ ሳይንስ ከሐምሌ 3-5 እንዲሁም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ከሐምሌ 9-11 በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል ተብሏል።
በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከሰኔ 30- ሐምሌ 01/2016 ድረስ እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ 6-7/2016 ወደ ዩኒቨርስቲ መግባት አለባቸው ሲል አሳስቧል።
ስለሆነም ተፈታኞች እና የሚመለከታቸው ሁሉ በወጣው ቀነገደብ መሰረት ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ እናሳስባለን ሲል አገልግሎቱ ባወጣው መረጃ ተናግሯል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: @ShegerFMRadio102_1
Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments