በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የቡግና ወረዳ ነዋሪ የምግብ ድጋፍ ካገኙ ከሀያ ቀን በላይ ሆኗቸዋል ተባለ፡፡
ከወራት በፊት በዞኑ ረሀብ ጠንቶ መክረሙን በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲነገር መቆየቱን ተከትሎ መንግስትም፣ ህዝቡም ሆነ ረጅ ድርጅቶች ድጋፍ ማድረግ እንደጀመሩ የሚዘነጋ አይደለም፡፡
ነገር ግን ከሀያ ቀናት በፊት በመንግስትም ሆነ በረጅ ድርጅቶች ይደረግ የነበረው ድጋፍ መቋረጡን የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ፅህፈት ቤት ነግሮናል፡፡
ባለፈው የክረምት ወቅት ባጋጠመ የዝናብ እጥረት የምርት አቅርቦት ችግር እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል በዚህም ደግሞ ነዋሪው ለምግብ እጥረት ተጋልጧል፡፡
አጠቃላይ አመርታለሁ ብሎ ካቀደው 294 ሺህ ኩንታል፤ 91 ሺህ ኩንታል ብቻ መመረቱ የተነገረ ሲሆን ይመረታል ተብሎ በእቅድ ከተያዘው 30 በመቶ ገደማው ብቻ እንደተገኘ የወረዳው የግብርና ፅህፈት ቤት መናገሩ የሚታወስ ነው፡፡
በዞኑ የተፈጠረውን የምግብ እጥረትም ለአለም ህዝብ እንዲደርስ በማድረግ እርዳታዎች ማግኘት ጀምረን ነበር የሚሉት የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አለሙ ይመር ድጋፉ ከተቋረጠም 20 ቀን አልፏል ይላሉ፡፡
ለዚህም አንደኛው ምክንያት የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID) ስራ ማቆሙ ነው ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል ክልሎች ራሳቸውን ችለው ችግር ያለባቸውን ነዋሪዎች ያግዙ በመባሉ ነው ተብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያንብቡ…
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comments