በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ያሉበት የዲፕሎማቲክ አጀባ(ኮንቮይ) ላይ የሽብር ጥቃት ተፈፀመ፡፡
አምባሳደር ጀማል በኸር ያሉበት የዲፕሎማቲክ ኮንቮይ ላይ ጥቃት የደረሰው በፓኪስታን ፓክቱንክዋ ክልል መሆኑንን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡
የዲፕሎማቲክ አጀቡ የሌሎች ሀገሮች ዲፕሎማቶች ያሉበት እንደነበርም ተጠቅሷል፡፡
የሽብር ጥቃቱን ያወገዘው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በጥቃቱም የኢትዮጵያ ዲፕሎማት ከሚያጅቡት ውስጥ አንደኛው ህይወቱ ማለፉን አስረድቷል፡፡
ጥቃቱን ያወገዘው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለፓኪስታን ህዝብ እና መንግስትም መፅናናትን እመኛለሁ ብሏል፡፡
በዲፕልማቶቹ ላይ የሽብር ጥቃት የተፈፀመባቸው ትናንት እሁድ በአካባቢው ያለን የቱሪስት ቦታ ለመጎብኘት ጉዞ ላይ በነበሩበት ወቅት መሆኑ ተሰምቷል፡፡
በቦምብ በተፈፀመው ጥቃት በዲፕሎማቶቹ ላይ ምንም ጉዳይ አልደረሰም ሲል ሮይተርስ የሀገሪቱን ባለስልጣናት ተጠቅሶ ዘግቧል፡፡
በመንገድ ላይ በተቀበረው ቦምብ ለተፈፀመው የሽብር ጥቃት ሀላፊነቱን የወሰደ ወገን የለም፡፡
ንጋቱ ሙሉ
Comments