top of page
የአካቶ ትምህርት ስርዓት ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች
መጋቢት 25/2018 በአካቶ ትምህርት ስርዓት አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች እንዳለባቸው ችግር ተለይተው እንደማንኛውም ሰው የትምህርት እድል እንዲያገኙ እየተደረገ ነው ቢባልም ልዩ ፍላጎት የሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ግን ጎዶሎዎች እንዳሉባቸው ይናገራሉ፡፡ በልዩ ፍላጎት የሰለጠነ በቂ መምህራን አለመኖር፣ የትምህርት ቁሳቁስ እጥረት፣ የመሰረተ ልማት ምቹ አለመሆንን ጨምሮ ሌሎች ችግሮች እንዳሉባቸው ያነሳሉ፡፡ ትምህርት ሚኒስቴርም በበኩሉ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የሚያነሱት ቅሬታ ትክክል ነው ለዚህ ደግሞ እንደ እኩዮቻቸው የትምህርት እድል እንዲያገኙ የአካቶ ትምህርት ሥርዓትን ዘርግቼ እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡ በተለይ የአካቶ ትምህርት ትግበራ ሲታሰብ የቁሳቁስ እጥረት፣ የሰለጠኑ መምህራን አለመኖር፣ የመሰረተ ልማት ምቹ አለመሆን በዋናነት የሚነሱ ጥያቄዎች
1 day ago


የተፈጠረውን የነዳጅ እጥረት ተከትሎ የጭነት መኪኖች ምልልስ በመቀነሱ የወጪ ንግዱ የሚላክበት ኮንቴይነር እጥረት ማጋጠሙ ተሰምቷል፡፡
መጋቢት 25/2018 በሀገር ውስጥ የተፈጠረውን የነዳጅ እጥረት ተከትሎ የጭነት መኪኖች ምልልስ በመቀነሱ የወጪ ንግዱ የሚላክበት ኮንቴይነር እጥረት ማጋጠሙ ተሰምቷል፡፡ በጅቡቲ የባዶ ኮንቴይነሮች ክምችት ቢጨምርም መኪኖች ወደ ሀገር ቤት በበቂ ሁኔታ ሊያመጧቸው ስላልቻሉ የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ድርጅት ባዶ ኮንቴነሮችን ወደ ሀገር እያስገባ እንደሚገኝ ነግሮናል። የኢትዮ ጁቡቲ ምድር ባቡር ድርጅት የቢዝነስ ደቨሎፕመንት እና የማርኬቲንግ ክፍል ሃላፊ ኤደን ተስፋዬ በተለይ በከፍተኛ የወጪ ንግድ ለተሰማሩ ድርጅቶች ቅድሚያ ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል። ላኪዎች ከድርጅቱ ጋር እንዲሰሩ እና በተፈጠረው ችግር ምክንያት መስተጓጎል እንዳይኖር እንዳያደርጉም ሃላፊዋ ጥሪ አቅርበዋል። ድርጅቱ ለወጪ ንግዱ ቅድሚያ በመስጠት ጭነቶችን ለማመላለስ ዝግጅት እንደጨረሰም ተ
1 day ago


የመካከለኛ ምስራቅ ጦርነት ያስከተለው የነዳጅ እጥረት አምራች ፋብሪካዎች ላይም ተፅዕኖ እያሳደረ ነው፡፡
መጋቢት 25/2018 የመካከለኛ ምስራቅ ጦርነት ያስከተለው የነዳጅ እጥረት አምራች ፋብሪካዎች ላይም ተፅዕኖ እያሳደረ ነው፡፡ የተለያዩ ምርቶችን ለገበያ የሚያቀርቡ ፋብሪካዎች በነዳጅ እጥረት ምክንያት ጥሬ እቃ ተወዶብናል ፣ ተፅዕኖዎቹን ተቋቁመን የምርት ሂደቱ እንዳይስተጓጎል ጥረት እያደረግን ነው ብለዋል፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ ኢራን ከአሜሪካና እስራኤል ጋር እያካሄደችው ያለው ጦርነት በእኛም ሀገር እንቅስቃሴዎች ላይ ተፅዕኖውን እያሳረፈ ነው። የትራንስፖርት ዘርፉ ተጠቃሽ ሲሆን አሁን ያለውን ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ የነዳጅ ግብይት መከተል እንደሚገባ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከሠሞኑ ማሳሰቡ ይታወሳል። የተፈጠረውን የነዳጅ አቅርቦት ችግር ተከትሎ በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ መስተጓጎል እንዳይፈጠር ፤ መንግስት ነዳጅን ከተጓዳኝ
2 days ago


የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በድጋሚ የአብረን እንስራ ጥሪ አቀረበ።
መጋቢት 25/2018 የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በድጋሚ የአብረን እንስራ ጥሪ አቀረበ። ላለፉት 3 ቀናት በአዲስ አበባ ከትግራይ ክልል ተወላጆች ጋር ሲካሄድ የቆየው የመጀመሪያ ዙር የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ዛሬ ተጠናቅቋል። በማጠናቀቂያው መርሃ ግብር መልዕክት ያስተላለፉት ፤ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የመከርነው ለትግራይ ሰላም እንጂ ትግራይን ለመጉዳት አይደለም፤ ከዚህም በኋላ አብሮ ለመስራት በራችን ክፍት ነው ሲሉ ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጥሪ አቅርበዋል። በምክክሩ የተነሱት ጉዳዮች ደረጃቸው ሊለያይ ይችል ይሆናል እንጂ፤ አብዛኞቹ በሁሉም ክልሎችና የከተማ መስተዳድር ከተነሱት ጋር ተቀራራቢ ናቸው ብለዋል። ይሁንና አንዳንዶቹ ጉዳዮች የትግራይ ብቻ የሆኑ መሆናቸውን አስተው
2 days ago


ዳሸን ባንክ ልዩ የሱፐር አፕ ማስተዋወቅ ውድድር ሽልማትን ጨምሮ አራት አዳዲስ አገልግሎቶችን ዛሬ አስጀመረ።
መጋቢት 24/2018 ዳሸን ባንክ ልዩ የሱፐር አፕ ማስተዋወቅ ውድድር ሽልማትን ጨምሮ አራት አዳዲስ አገልግሎቶችን ዛሬ አስጀመረ። ባንኩ የሱፐር አፕ ተጠቃሚዎችን ለማበረታት እንዲሁም የአገልግሎቱን ተደራሽነት ለማስፋት የቲክቶክ ይዘት ፈጠራ ውድድር ማዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል። በዚህ ውድድር ለሚያሸንፉ የይዘት ፈጣሪዎች በድምሩ ስድስት ሚሊዮን ብር የገንዘብ ሽልማት እንዳዘጋጀ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የንግድ ሥራ ትምህርት ቤት (ኮሜርስ) በተዘጋጀ ስነ ስርአት ላይ ተነግሯል። በዳሸን ሱፐር አፕ ቲክቶክ ቻሌንጅ አሸናፊ ለመሆን ይዘት ፈጣሪዎች ስለ ዳሸን ባንክ ሱፐር አገልግሎቶች የሚገልፅ የቲክቶክ ቪዲዮ በመስራት ማጋራት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል። የሰሩት ቪዲዮ በቲክቶክ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዕይታ ሲያገኝ፣ በዳሸን ሱፐር አፕ ውስጥ በሚገኘው የዳሸን ክሬቲቭ አ
2 days ago


ከቴምር ፕሮፐርቲ መኖሪያ ቤት የሚገዙ ደንበኞች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ልዩ የሼባ ማይልስ ስጦታ የሚያገኙበት ዕድል መዘጋጀቱ ተነገረ።
መጋቢት 24/2018 ከቴምር ፕሮፐርቲ መኖሪያ ቤት የሚገዙ ደንበኞች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ልዩ የሼባ ማይልስ ስጦታ የሚያገኙበት ዕድል መዘጋጀቱ ተነገረ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የደንበኞች ሎያሊቲ ክፍል ማናጀር አቶ ሰለሞን መኮንን እና የቴምር ፕሮፐርቲ የኢቨንት እና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር አቶ ዑስማን መሀመድ ስምምነቱን በሰጡት መግለጫ ይፋ አድርገዋል። በዚህ ስምምነት መሰረት የቴምር ሪል ስቴት ደንበኞች የሚገዙትን የቤት ወይም የሱቅ አይነት መሰረት ያደረገና የከፈሉትን መጠን ያማከለ የዓለም አቀፍ በረራ የማይልስ ዕድል ያገኛሉ ተብሏል። የቴምር ደንበኞች በዚህ ስምምነት መነሻነት የሼባማይልስ ደረጃቸው እንደ ክፍያቸው ሁኔታ እያደገ የሚሄድ ሲሆን፤ ከብሉ ወደ ሲልቨር፣ ከሲልቨር ወደ ጎልድ ወይም ከብሉ ወደ ጎልድ የማሳደግ ዕድልንም ይሰጣል መባሉን ሰም
2 days ago


ቪዛ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለ ቪዛ ካርድ ደንበኞች የ2026 የዓለም ዋንጫን በአካል ተገኝተው የሚመለከቱበትን ዕድል ይዘው መቅረባቸውን ተናገሩ።
መጋቢት 24/2018 ቪዛ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለ ቪዛ ካርድ ደንበኞች የ2026 የዓለም ዋንጫን በአካል ተገኝተው የሚመለከቱበትን ዕድል ይዘው መቅረባቸውን ተናገሩ። ዕድሉ የምድብ ጨዋታዎችን በአካል ለመመልከት የሚያስችል መሆኑ ተነግሯል። ይህ ከመጋቢት 5 እስከ ሚያዝያ 6 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ንቅናቄ፣ በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ የባንኩ የዴቢትም ሆነ የቅድመ ክፍያ ቪዛ ካርድ ተጠቃሚዎች በሙሉ ክፍት ነው ተብሏል። ደንበኞቹ በቪዛ ካርዳቸው የሚፈጽሙት እያንዳንዱ ግብይት እንደ አንድ ዕጣ ይቆጠራል የተባለ ሲሆን ለዚህ ምዝገባ አይጠየቅም ተብሏል። በቪዛ የምሥራቅ አፍሪካ ክላስተር ሓላፊ የሆኑት ያሬድ እንዳለ፣ የካርድ ተጠቃሚዎችን በየቀኑ እየፈጸሟቸው ለሚገኙ ግብይቶች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ተባብረን በመሸለማችን ደስተኞች ነን'' ብለዋል።
2 days ago


አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ከሌሎች ተማሪዎች እኩል የማይማሯቸው ትምህርቶች በመኖራቸው ተወዳዳሪነታችንን ይቀንስብናል ብለዋል።
መጋቢት 24/2018 በኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ቀላል የማይባል ችግር እንደሚያጋጥማቸው በተደጋጋሚ ይናገራሉ፡፡ የመሰረተ ልማት አለመሟላት፣ እነሱን ተቀብሎ የሚያስተምር ትምህርት ቤት አለማግኘት፣ የቁሳቁስ አለመሟላት፣ በስራ ቅጥር ወቅት እድል አለማግኘት እና በሌሎች ፈተናዎች እንደሚያልፉ ይነገራል፡፡ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ከሌሎች ተማሪዎች እኩል የማይማሯቸው ትምህርቶች በመኖራቸው ተወዳዳሪነታችንን ይቀንስብናል ብለዋል። በዚህም ምክንያት አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ገበያ ሲቀላቀሉ ከሌሎች ተማሪዎች ጋር እኩል ተወዳዳሪ ለመሆን እንደሚቸገሩ አንስተዋል። ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ እስከ ሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ክፍል ድረስ አካል ጉዳተኞች የማይማሯቸው የትምህርት ዓይነቶች በመኖራቸው ተወዳዳሪነታቸው ላይ ችግር እየፈጠረባቸው
2 days ago


ታሪክን የኋሊት - ንግስተ ነገስታት ንግስት ዘውዲቱ
በኢትዮጵያ የመሪዎች ታሪክ ፣ ባለፉት 1000 ዓመታት ውስጥ የመጀመሪያዋ ሴት ንግስተ ነገስታት የነበሩት ንግስት ዘውዲቱ ፣ ያረፉት በ1922 ዓ.ም በዛሬው ቀን ነበር፡፡ ንግስተ ነገስታት ዘውዲቱ፣ በ10ኛ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ መሪ እንደነበረች ከሚነገርላት ዮዲት ጉዲት ወዲህ ፣ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሴት መሪ ነበሩ፡፡ ንግስት ዘውዲቱ ፣ የኢትዮጵያን ንግስና ያገኙት ፣ በጊዜው የነበሩት የጦር አለቆች ፣ አገረ ገዥዎች ፣ መኳንንት የቤተ መንግስቱ የጥበቃ ወታደሮች ምርጫ እንጂ እንደቀደምቶቻቸው በውርስና በውጊያ አልነበረም፡፡ ከአዲስ አበባ ቤተ መንግስት የተላኩ የጦር መኮንኖች ፣ መሳፍንቱ መኳንንቱ ሕዝብና ሰራዊት፣ በአንድነት ተስማምተው ፣ ነግስተ ነገስታት ዘውዲቱ ተብለው ፣ በአባትዋ በአፄ ምኒልክ ዙፋን እንዲቀመጡ “መርጦዎታል” ተብለው የተነገሩት
2 days ago



Facebook
Twitter
Pinterest
Tumblr
Copy Link
Link Copied
Search video...

Now Playing
እስራኤል እና አሜሪካ ጦርነት አቁመው ከኢራን ጋር የስምምነት ፊርማ የሚያኖሩት መቼ ይሆን #Mamuasha #ማሟሻ
10:52

Now Playing
በአዲስ አበባ የመንግስት ሰራተኞች ለአደጋ ቅነሳ በሚል ከደመወዛቸው የመቆረጡ ጉዳይ
05:21

Now Playing
አየርላንድ ኢምባሲ ሴንት ፓትሪክ ቀንን በባህላዊ የሙዚቃ መሳሪዎች ከያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ጋር በመሆን ያካሄዱት ዝግጅት Saint Patrick’s Day!
48:15

Now Playing
ለአእምሮ ጤና እክል አጋላጭ የሆኑ የስራ ዘርፎች የትኞቹ ናቸው፣ምን ጥንቃቄ ማድረግስ ይገባል?
05:40

Now Playing
አልሰማንም እንዳትሉ - እናት ማናት?
05:56

Now Playing
መቆያ - ሞትን የናቀው ጦረኛ - ድራር አልዘዋር - በእሸቴ አሰፋ #shegerfm #mekoya
24:28

Now Playing
መዓዛ ብሩ ከዶ/ር ተካልኝ ወልደማርያም እና ዶ/ር ዮናስ አሽኔ ጋር የተደረገ ወግ መጋቢት 13/ 2018
40:57

Now Playing
ትዝታ ዘአራዳ - የጣሊያን ዘር ከሀበሻ ዘር እንዳይደባለቅ ይደነግግ የነበረው አዋጅ
20:46
bottom of page

