top of page

ጳጉሜ 5 2017 - የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በቅርቡ በአዲስ አበባ እና ዙሪያ መውጫ በሮች ላይ ድንገተኛ የተሽከርካሪዎች የቴክኒክ ፍተሻ ጉዳይ

  • sheger1021fm
  • Sep 10, 2025
  • 1 min read

በቅርቡ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ከተሽከርካሪዎች የቴክኒክ ብቃት ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ እና ዙሪያ መውጫ በሮች ላይ ድንገተኛ የተሽከርካሪዎች የቴክኒክ ፍተሻ አድርጓል፡፡


ይህም በተለይ አሮጌ ተሽከርካሪዎችን ከከተማ ለማስወጣት የተደረገ ነው በሚል ቅሬታ ሲቀርብ ነበር፡፡


የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በበኩሉ የቴክኒክ ብቃት ፍተሻው የተደረገው ከደህንነት አንፃር እንጂ ሌላ ዓላማ ኖሮት አይደለም ብሏል፡፡


በትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር የትራንስፖርት አገልግሎትና ቁጥጥር ዘርፍ አማካሪ አቶ አሰፋ ሃዲስ በተሽከርካሪዎች ላይ ያደረግነው ክትትልና ድጋፍ የተካሄደው ተሽከርካሪዎችን የእድሜ ዘመን በመመልከት ከሚደርስ አደጋ እንዲሁም ተሽከርካሪዎቹ በቂ ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ ስለማድረጋቸው ለማረጋገጥ እንጂ ሌላ ዓላማ ኖሮት አይደለም ብለዋል፡፡


ከቴክኒክ ብቃት ቁጥጥር ጋር በተያያዘ ያለው ስራ በመጭው ዓመትም እንደሚቀጥል የሚናገሩት አቶ አሰፋ ይህም በተሽከርካሪዎች የቴክኒክ ብቃት ችግር ምክንያት የሚደርስ የትራፊክ አደጋ መጠን በመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ ጉዳዩ ለድርድር የማይቀርብ ነው ብለዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….


ምህረት ስዩም


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page