ጳጉሜ 5 2017 - በ2018 ታጣቂዎች በምክክር ሂደት እንዲሳተፉ ለማድረግ ማቀዱን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናገረ።
- sheger1021fm
- Sep 10, 2025
- 1 min read
ከህዝብ የተሰበሰቡ አጀንዳዎችም በአዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያውያን ይፋ ይደረጋሉ ተብሏል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ይህን ያለው ለጋዜጠኞች ዛሬ በዋና መስሪያ ቤቱ በሰጠው መግለጫ ነው።
በተጠናቀቀው የ2017 ዓ.ም ኮሚሽኑ ስኬታማ ያላቸውን ስራዎች መሰራቱን የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ ተናግረዋል።
በአዲሱ ዓመት 2018 በ6 ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ኮሚሽኑ ለመስራት ማቀዱን ቃል አቀባይዉ ለጋዜጠኞች አስረድተዋል።

በምክክር ሂደቱ አስካሁን ያልተሳተፉ እና ሲሳተፉ ቆይተው በተለያዩ ምክንያቶች ያቋረጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም በትጥቅ ትግል ያሉ ሀይሎችና ሌሎች ወደ ምክክር መድረኩ እንዲመጡ ለማድረግ የተጀመሩ ጥረቶች በ2018ም ይቀጥላሉ ሲሉ አቶ ጥበቡ ተናግረዋል።
የአጀንዳ ቀረጻ ሥራውን በማከናወን ምክክር የሚደረግባቸው እና ሌሎች አጀንዳዎችን ለህዝብ ይፋ ይደረጋሉ ያሉት አቶ ጥበቡ በተመረጡ አጀንዳዎች ላይም ምክክር እንዲካሄድ ከመግባባት እንዲደረስ ይሰራል ብለዋል።
መግባባት የተደረሰባቸው ጉዳዮችም ተፈጻሚ እንዲሆኑ ምክረ ሃሳቦችን በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካል ያቀርባል ሲሉ አቶ ጥበቡ ጠቁመዋል።
የትግራይ ክልል በምክክር ሂደቱ እንዲካተት ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት እንደሚሰራም አስረድተዋል።
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments