top of page

ጳጉሜ 4 2017 - በኢትዮጵያ የቡና እርሻን ከዛፍ ጥላ ውጪ ማሰብ አልተለመደም

  • sheger1021fm
  • Sep 9, 2025
  • 1 min read

ቡና ጥላ ይወዳል ሲባልም ይሰማል። ኢትዮጵያ በዚህ መንገድ ቡናን እያመረተች ለውጪ ገበያ ታቀርባለች።


ከአንድ ሄክትር የሚገኘው የቡና ምርትም ከ7 እስከ 9 ኩንታል እንደሆነ መንግስት ይናገራል።


በኢትዮጵያ የቡና ምርት እና የወጪ ንግድ ከቀዳሚዎቹ የሆነው ቀርጫንሼ ግሩፕ ይህንን መንገድ በመቀየር ቀዳሚ ሆኗል።


ከብራዚል ያስመጣውን የቡና ዘር ከዛፍ ጥላ ውጪ በሰፊ እርሻ በመትከል የሚገኘውን ምርት በሄክትር እስከ 62 ኩንታል አድርሶታል።


ከሰሞኑ በምእራብ ጉጂ ገላና ጌሻ እርሻው በዚህ መንገድ ያለማው 750 ሄክታር የቡና እርሻ ተጎብኝቷል።


በዚህ የግብርና ቴክኖሎጂ ቀርጫንሼ ግሩፕ ለውሃ አቅርቦት የእስራኤልን የጠብታ ውሃ ቴክኖሎጂን ይጠቀማል።


የግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ አረጋ ይህ ቀርጫንሼ ብዙ ሙከራዎችን በማድረግ ከ8 ዓመት ልፋት በኋላ የደረሰበት ውጤት በሀገር ደረጃ ቡና የምናመርትበትን መንገድ እንድንቀይር አዲስ መንገድን ያሳየን ነው ብለዋል።


በዓለም ዙሪያ ቀዳሚ የሆኑ ቡና አምራቾች በዚህ መንገድ ቡናን በከፍተኛ መጠን እያመረቱ ለዓለም ለገበያ እንደሚያቀርቡም ተናግረዋል።


የቀርጫንሼ ግሩፕ ቀዳሚ ሆኖ ያስተዋወቀው ቡናን ከዛፍ ጥላ ውጪ በሰፊ እርሻ መትከል በሄክታር የሚገኘው የቡና ምርትን ከሰባት እጥፍ በላይ እንዳሳደገው ተነግሯል።


በዓመት 65,000 ቶን ቡና ለአለም ገበያ እንደሚያቀርብ የተናገረው ቀርጫንሼ ግሩፕ የቡና ምርታማነት ለማሳደግ ከዲላ ዩኒቨርስቲ ጋር በትብብር የምርምር ስራን እየሰራ መሆኑም ተነግሯል።


ስምምነቱ  በሽታ እና ድርቅ የሚቋቋሙ የቡና ዝርያዎችን በማውጣት ምርትና ምርታማነት ለመጨመር ያለመ መሆኑ ተነግሯል፡፡


ቴዎድሮስ ወርቁ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




1 Comment


Neha Meena
Neha Meena
Sep 10, 2025

Elegance often comes with maturity and charm, which is why we provide a special Escort Service In Aerocity. These companions offer warmth, sensuality, and sophistication, making each meeting feel genuine and personal. At Nehameena, we carefully arrange experiences that balance intimacy with discretion, ensuring your comfort at all times. Whether you seek romance, companionship, or relaxation, our escorts provide moments that are memorable, natural, and deeply satisfying, tailored to your unique desires.

Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page