ጳጉሜ 3 2017 - ከ2018 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች፤ ተማሪዎች ኤሌክትሮኒክስ ቁሰቀቁሶችን ይዘው ት/ቤት እንዳይሄዱ ተከለከለ
- sheger1021fm
- Sep 8
- 1 min read
ከ2018 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች፤ ተማሪዎች ሞባይል ስልክ፣ ታብሌትና ኤሌክትሮኒክስ ቁሰቀቁሶችን ይዘው ወደ ትምህርት ቤት እንዳይሄዱ ተከለከለ።
ይህን ያለው የትምህርት ሚኒስቴር ነው።
በ2018 ዓ.ም ትምህርት ቤቶች ከመስከረም 05/2018 ዓ.ም ጀምሮ የመማር ማስተማር ሥራ ይጀምራሉ ሲልም የትምህርት ሚኒስቴር አስረድቷል።
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ የ2018 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ ሰኞ መስከረም 5/ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ይጀመራል ማለታቸውን ከመ/ቤቱ ማህበራዊ የትስስር ገፅ ላይ ተመልክተናል።
ዓርብ መስከረም 2/2018 ዓ.ም ትምህርት ቤቶች ክፍት ሆነው መምህራንና ተማሪዎች ውይይት የሚያደርጉበትና መስከረም 5/2018 ዓ.ም በይፋ ለሚጀመረው የትምህርት ስራ ቅድመ ዝግጅት የሚያደርጉበት ቀን መሆኑንም ወ/ሮ አየለች አስረድተዋል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s











Comments