top of page

ጥር 21 2017 - የአለም ሎሬት ሜተር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ መኖሪያ እና ስቲዲዮ የነበረው ቪላ አልፋ ከአራት ወራት ብኋላ ለህዝብ ክፍት ሊደረግ ነው

  • sheger1021fm
  • Jan 29
  • 1 min read

የአለም ሎሬት ሜተር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ መኖሪያ እና ስቲዲዮ የነበረው ቪላ አልፋ ከአራት ወራት ብኋላ ለህዝብ ክፍት ሊደረግ ነው።


በአዲስ አበባ ጦር ሀይሎች አካባቢ የሚገኘው ቪላ አልፋ ከጣሪያው ጀምሮ ወደ ምድር የሚዘልቀው ፍሳሽ የእድሳት ጉዞውን ረጅም እና እድካሚ እንዳደረገው ታውቋል።


ነገር ግን በሁለት ወር ውስጥ ቀሪው ስራ እና የሙዚየም ስራው ተጠናቆ በአራት ወር ውስጥ ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባ አያሌው ነግረውናል።

ree

ህዝብ በጉጉት ሲጠብቀው የነበረው የአርቲስቱ መኖሪያ ቪላ አልፋ ከዛሬ ነገ በቅርቡ ክፍት ይሆናል ሲባል ቆይቷል።


ለመሆኑ ከወሰን ማካለል እና አካባቢው መኖሪያ መሃል እንደመሆኑ መጠን በዚህ ሐሳብ መንገድ ምን ተሰራ ብለን የጠየቅናቸው ኃላፊው የሙዚየሙ አጎራባች እንደተለየና ለጉብኝት አመቺ ተደርጎ እንደታደሰ ነግረውናል።


የአለም ሊቀ ሊቃውንት የኪነ ጥበብ ባለሙያው ሰአሊ አፈወርቅ ተክሌ የእጅ ስራዎች መካከል መናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የግድግዳና ጣሪያ ስዕሎች፣ የሞዛይክ ስራዎች፣ የመስኮትና መስታወት ስዕሎች፣ የዳግማዊ የምፅአት ፍርድ፣ የደመራ ስእል፣ የራስ መኮንን ሀውልት፣ የአፍሪካ ድል አፍሪካ አጠቃላይ ነጻነት፣ የመስቀል አበባ እንዲሁም እናት ኢትዮጵያ ይገኙበታል።



ተህቦ ንጉሴ

Recent Posts

See All
ወደ ቀድሞ ቀያቸው ሄደው እንደገና ወደ ደብረብርሃን የተመለሱ ተፈናቃዮች መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡ 

ታህሳስ 11/2018   ወደ ቀድሞ ቀያቸው ሄደው እንደገና ወደ ደብረብርሃን የተመለሱ ተፈናቃዮች መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡   የአማራ ክልል የአደጋ ስጋት መስሪያ ቤት በጉዳዩ ላይ መልስ ለመስጠት አልፈቀደም።   ከመንግስት የሚቀርበውን ድጋፍ ለተፈናቃዮች የሚያከፋፍለውና ሌሎች ስራዎችን የሚሰራው በመንግስት የተቋቋመ ኮሚ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page