top of page

ጥር 20 2017 - በተለያዩ አካባቢዎች 75 አባላቶቹ እንደታሰሩ ኢዜማ ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Jan 28
  • 1 min read

በተለያዩ አካባቢዎች 75 አባላቶቹ እንደታሰሩ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ተናገረ፡፡


እየተፈፀመ ያለው ውክቢያና እስር ሰላማዊ ትግሉን አደጋ ላይ የሚጥልና ወደ ሌላ አማራጭ የሚገፋ ነው ሲል ተናግሯል፡፡


ኢዜማ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የታሰሩ አባላቶቹ በአፋጣኝ እንዲፈቱለም ጠይቋል፡፡


ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ከ5 ወር በላይ የቆዩ መኖራቸውንም ፓርቲው ተናግሯል፡፡


የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ኢዜማ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የታሰሩ አባላቶቹ ላይ የሚፈፀመው ውክቢያ ሊቆም ይገባል ሲል አሳስቧል፡፡


ፓርቲው እየተፈፀሙ ያሉ እስራቶች እና ውክቢያዎች ወደ ቀድሞ አዙሪት የሚከቱ ስለሆነ ሰላማዊ ትግል በሚያራምዱ አባላቶቹ ላይ የሚፈፀመው እስር ሊቆም ይገባል ብሏል፡፡


የኢዜማ የህግ እና አባላት ደህንነት መምሪያ ሀላፊ የሆኑት አቶ ስዩም መንገሻ አሁን በፓርቲው አባላቶች ላይ እየተፈፀሙ ያሉ እስራት እና ውክቢያዎች ሰላማዊ ትግሉን አደጋ ላይ የሚጥሉና ሌላ አማራጭ እንድናይ የሚገፋ ነው ሲሉ ነግረውናል፡፡

ree

ኢዜማ ስሜታዊነት የሚያጠቃው ፓርቲ እንዳልሆነ ይታወቃል ያሉት አቶ ስዩም በዚህም እቅድ ነው እየሰራን ያለው ብለዋል፡፡


“እዚህ አገር ላይ በምክንያት፣ በሀሳብ የበላይነት የፖለቲካ ውድድር ተደርጎ መንግስት በዚያ መንገድ ነው መለወጥ ያለበት ብሎ አምኖ እየታገለ ያለ ፓርቲ  ነው'' ያሉት የኢዜማ የህግ እና አባላት ደህንነት መምሪያ ሀላፊ የሆኑት አቶ ስዩም መንገሻ ይሁንና አሁን እየተፈፀሙ ያሉ ድርጊቶች ግን ሌላ አማራጭ እንድናይ የሚያስገድድ ነው ብለዋል፡፡


ይሁንና የፖለቲካ አባላቶችን በየቦታው ባንገላታን ቁጥር የሚመጣው የፖለቲካ ምህዳር መጥበብ ነው የዲሞክራሲ ሒደትን ማቆም ነው ስለዚህ ከዚህ ችግር ለመውጣት ደግሞ የሰላማዊ ትግል አራማጆች ላይ የሚፈፀሙ ውክቢያዎች እና እስራቶች ሊቆሙ ይገባል የታሰሩትም መፈታት አለባቸው ብለዋል፡፡


የፖለቲካ ምህዳሩ በጠበበ ቁጥር የፖለቲካ ፓርቲዎች በፖለቲካው ሜዳ ላይ እንዲጫወቱ የሚያደርጉ ሒደቶች ይደነቃቀፋሉ ይህ ደግሞ መልሶ ወደ ቀድሞ አዙሪት ይከተናል ብለዋል፡፡


እዚህ አገር ላይ የነበረው በጦርነት ወይም በአብዮት ነው ይህ ነገር ይቁም ከተባለ ደግሞ በሀሳብ የበላይነት መሆን አለበት የፖለቲካ ምህዳሩ መስፋት አለበት የመደራጀት መብትም መፈቀድ አለበት ብለዋል፡፡


ያሬድ እንዳሻው

 
 
 

Recent Posts

See All
ወደ ቀድሞ ቀያቸው ሄደው እንደገና ወደ ደብረብርሃን የተመለሱ ተፈናቃዮች መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡ 

ታህሳስ 11/2018   ወደ ቀድሞ ቀያቸው ሄደው እንደገና ወደ ደብረብርሃን የተመለሱ ተፈናቃዮች መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡   የአማራ ክልል የአደጋ ስጋት መስሪያ ቤት በጉዳዩ ላይ መልስ ለመስጠት አልፈቀደም።   ከመንግስት የሚቀርበውን ድጋፍ ለተፈናቃዮች የሚያከፋፍለውና ሌሎች ስራዎችን የሚሰራው በመንግስት የተቋቋመ ኮሚ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page