ጥር 19 2017 - የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባኤን በማስመልከት የፓርቲው ም/ል ፕሬዘዳንት አደም ፋራህ መግለጫ ሰጥተዋል
- sheger1021fm
- Jan 27
- 1 min read
ከቀናት በኋላ በአዲስ አበባ የሚካሄደውን #የብልፅግና_ፓርቲ ሁለተኛ ጉባኤን በማስመልከት የፓርቲው ምክትል ፕሬዘዳንት አደም ፋራህ ዛሬ ለጋዜጠኞች ጠቅለል ያለ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በአባላት ብዛት ፓርቲያቸው በአለም ላይ ከአንድ እስከ አስረኛ ደረጃ ከያዙ ፓርቲዎች አንዱ መሆኑንና በአሁኑ ወቅት ከ15.7 ሚሊዮን አባላት በላይ መያዙን ፓርቲው ምክትል ፕሬዘዳንት ተናግረዋል፡፡

ከ1,700 በላይ አባላቱ በፓርቲው ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ የተባለ ሲሆን ከ15 የማያንሱ የውጪ ሀገር ፓርቲዎችም በጉባኤ ላይ ለመገኘት እሽታቸውን መስጠታቸውንም አደም ፋራህ ተናግረዋል፡፡
“ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ቃል የፓርቲው ሁለተኛ ጉባኤ በአዲስ አበባው አደዋ አዳራሽ ለሁለት ቀናት ይደረጋል ያሉት የፓርቲው ምክትል ፕሬዘዳንት ከጉባኤ የተለያዩ ውጤቶች ይጠበቃል ብለዋል፡፡
የብልፅግና ፓርቲን ሁለተኛ ጉባኤን መሰረተት በማድረግ በተሰጠው መግለጫ ላይ፤ ጋዜጠኞች ጥያቄ መጠየቅ እንደማይችሉ በመነገሩ ከጉባኤው እና ከአጠቃላይ ከፓርቲው ጋር የተያያዙ ነጥቦችን በዚህ ወሬአችን ማካተት አልቻልንም፡፡
የኔነህ ሲሳይ











Comments