ጥር 19፣2017 - የሴቶች ጥቃት ተደጋግሞ በመሰማቱም የየዕለት ተግባር የሆነ ይመስላል ምን ይሻላል?
- sheger1021fm
- Jan 27
- 1 min read
በቤተሰብ አባል፣ በአባት፣ በወንድም የአስገድዶ መደፈር ወንጀል የሚፈጸምባቸው በወንድ ጓደኞቻቸው እና የትዳር አጋር ከባድ የአካል ጉዳትና እስከሞት የደረሰ ጉዳት የሚደርስባቸው ሴቶች ቁጥር በርክቷል፡፡
ወንጀሉ ተደጋግሞ በመሰማቱም የየዕለት ተግባር የሆነ ይመስላል፡፡
ይህ በሴቶች ላይ የሚፈጸመው የ #ጾታዊ_ጥቃት ወንጀል እንዲህ ተደጋግሞ ቢሰማም በአግባቡ በህግ ፊት ተጠያቂ የሚሆኑት ወንጀለኞች ግን ተገቢውን ቅጣት ሲያገኙ አይታይም፡፡
ይህም ወንጀሉ የተለመደ ይመስል እንዲደጋገም እያደረገ ነው ለዚህም የሀገሪቱ የወንጀል ህግ በአጥፊዎች ላይ የሚጥለው ቅጣት በቂ ባለመሆኑ ነው ሲሉ የስርዓተ ጾታ መብት ተሟጋቾች እና የህግ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
ከሀና ላላንጎ እስከ ህፃን ሄቨን በሴቶች በህፃናት ላይ የተፈፀሙ፣ ለጆሮ የሚከብዱ ጥቃቶች በተደጋጋሚ እያጋጠመ ነው፡፡
ለጥቃቱ መጨመር በአጥፊዎቹ ላይ የሚጣለው ቅጣት አነስተኛ መሆኑ ነው በሚል ይነሳል፡፡
ታድያ ምን ይሻላል?
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5rs











Comments